إعدادات العرض
አግራሩ አታክብዱ! አበስሩ አታሽሹ!
አግራሩ አታክብዱ! አበስሩ አታሽሹ!
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "አግራሩ አታክብዱ! አበስሩ አታሽሹ!"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
ar bn bs en es fa fr id ru tl tr ur zh hi si ug ku ha pt ml te my th de ja ps vi as sq sv cs gu yo nl sw ta prs hu kn ky lt mg ro rw ne sr so mos uk bg wo az ka tg bm mk om kmالشرح
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሁሉም ዓለማዊም ይሁን ዲናዊ በሆኑ ጉዳዮች ለሰዎች ማቅለልና ማግራራትን እንዲሁም እነርሱ ላይ አለማክበድን አዘዙ። ይህም ማግራራት አላህ በፈቀደውና በደነገገው ድንበር ውስጥ ሆኖ ነው። ሰዎችን በመልካም ነገሮች በማበሰርና እነርሱን ከመልካም ነገሮች ባለማሸሽ ላይም አበረታቱ።فوائد الحديث
የአንድ አማኝ ግዴታ ሰዎች አላህን እንዲወዱ ማድረግና በመልካም ነገሮች ላይ ማነሳሳት ነው።
ወደ አላህ የሚጣራ ሰው የኢስላምን ጥሪ ወደ ሰዎች በጥበብ እንዴት እንደሚያደርስ ማስተዋል ይገባዋል።
ማበሰር ለዳዒውም ለሚያስተላልፈው ነገርም ደስታን ተሰሚነትንና መረጋጋትን ያስተርፋል።
ማካበድ በዳዒው ንግግር ውስጥ ማሸሽን ፣ ተቀባይነት ማጣትና ጥርጣሬን ይፈጥራል።
ለነርሱ የወደደላቸው ገር እምነትና ቀላል ድንጋጌ በመሆኑ አላህ በባሮቹ ላይ ያለው እዝነት ሰፊ መሆኑን እንረዳለን።
እንድናግራራ የታዘዝንባቸውን ነገሮች ማግራራት ሸሪዓ ይዞት የመጣው አንዱ ድንጋጌ ነው።
التصنيفات
ምስጉን ስነ-ምግባር