إعدادات العرض
ፍትሃዊዎች (የትንሳኤ ቀን) አላህ ዘንድ በብርሃን በተሰራ ወንበር ላይ ከአርራሕማን ቀኝ በኩል ይሆናሉ። ሁለቱም የአላህ እጆች ቀኝ ናቸው።
ፍትሃዊዎች (የትንሳኤ ቀን) አላህ ዘንድ በብርሃን በተሰራ ወንበር ላይ ከአርራሕማን ቀኝ በኩል ይሆናሉ። ሁለቱም የአላህ እጆች ቀኝ ናቸው።
ከዐብደላህ ቢን ዐምር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ፦ የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦ "ፍትሃዊዎች (የትንሳኤ ቀን) አላህ ዘንድ በብርሃን በተሰራ ወንበር ላይ ከአርራሕማን ቀኝ በኩል ይሆናሉ። ሁለቱም የአላህ እጆች ቀኝ ናቸው። (ፍትሃዊ የሚባሉትም) እነዚያ በፍርዳቸው፣ በቤተሰቦቻቸውና በተሾሙበት ጉዳዮች ላይ ፍትህን የሚያሰፍኑ ናቸው።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी සිංහල Kurdî Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە Hausa ไทย دری Fulfulde Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių or Română Kinyarwanda Српски O‘zbek Moore नेपाली Malagasy тоҷикӣ Oromoo Wolof Soomaali Български Українська Azərbaycan ქართული bm Македонскиالشرح
እነዚያ በአመራራቸውና በፍርዳቸው ስር ያሉ ሰዎችን እና በቤተሰቦቻቸው መካከል በፍትህና በእውነት የሚፈርዱ ሰዎች የትንሳኤ ቀን ለነሱ ክብር ይሆን ዘንድ ከፍ ባሉ ከብርሃን የተፈጠሩ ወንበሮች ላይ እንደሚቀመጡ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ። እነዚህም ወንበሮች በአርራሕማን ቀኝ በኩል የሚገኙ ናቸው። ጥራት የተገባው አላህ ሁለቱም እጆቹ ቀኝ ናቸው።فوائد الحديث
የፍትህ ትሩፋቱና በሱ ላይ መበረታታቱ፤
ፍትህ በሰዎች መካከል ያሉ ሁሉንም ፍርድና ኃላፊነትን የሚያካትት ጠቅላይ ቃል ነው። በሚስቶች፣ በልጆችና በሌሎችም መካከል ፍትህ ማስፈን ሳይቀር ፍትሃዊነት ውስጥ ይገባል።
የትንሳኤ ቀን የፍትሃዊዎች ደረጃ መገለፁን ፤
የትንሳኤ ቀን የኢማን ባለቤቶች ደረጃ የሚበላለጥ መሆኑን ፤ ሁሉም በስራው ልክ ነውና የሚመነዳው።
በማነሳሳት ማስተማር ዘይቤ የሚማሩትን ሰዎች ትምህርቱን እንዲቀበሉ የሚያነሳሳ ከሆኑት የማስተማር ዘይቤዎች መካከል መሆኑን እንረዳለን።
التصنيفات
ምስጉን ስነ-ምግባር