إعدادات العرض
ሟቾችን አትሳደቡ! እነርሱ ወዳስቀደሙት (ስራቸው) ሂደዋልና።
ሟቾችን አትሳደቡ! እነርሱ ወዳስቀደሙት (ስራቸው) ሂደዋልና።
ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ሟቾችን አትሳደቡ! እነርሱ ወዳስቀደሙት (ስራቸው) ሂደዋልና።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]
الترجمة
ar bn bs en es fa fr id ru tl tr ur zh hi vi ku ha pt ml te sw my de ja ps as sq sv cs gu yo nl ug si ta prs ff hu kn ky lt or ro rw sr uz mos ne wo so bg uk az ka tg bm mk el km mg omالشرح
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሟቾችን መሳደብና ክብራቸውን መንካት ክልክል መሆኑን አብራሩ። ከእኩይ ስነ ምግባሮችም የሚመደብ እንደሆነ ገለፁ። ምክንያቱም ይህ ስድብ በህይወት ያሉ ሰዎችን ከመጉዳት በዘለለ ለነርሱ የማይደርሳቸው ከመሆኑም በተጨማሪ እነርሱ ወዳስቀደሙት መልካምም ይሁን መጥፎ ስራቸው ደርሰዋልና።فوائد الحديث
ሐዱሡ ሟቾችን መሳደብ ክልክል መሆኑን ይጠቁማል።
ሟቾችን ከመሳደብ መታቀብ የህያው ሰዎችን ጥቅምም የማህበረሰቡንም ሰላም ከመጣላትና ከመናቆር ይጠብቃል።
ሟቾችን ከመሳደብ የመከልከሉ ጥበብ ወዳስቀደሙት ስራ ስለደረሱ መስደቡ ከንቱ ስለሆነና በተጨማሪ የህያው ቅርብ ዘመዶቹን ስለሚያውክ ነው።
የሰው ልጅ ጥቅም የሌለውን ነገር መናገር አይገባውም።