إعدادات العرض
አላህ በሁሉም ነገሮች ላይ ኢሕሳን (እንድናሳምር) ፅፏል።
አላህ በሁሉም ነገሮች ላይ ኢሕሳን (እንድናሳምር) ፅፏል።
ከሸዳድ ቢን አውስ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተዘገበው እንዲህ አሉ: ሁለቱን ከአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ንግግር ሸምድጃለሁ፦ "አላህ በሁሉም ነገሮች ላይ ኢሕሳን (እንድናሳምር) ፅፏል። የገደላችሁ ጊዜ አገዳደላችሁን አሳምሩ፤ ያረዳችሁም ጊዜ አስተራረዳችሁን አሳምሩ። አንዳችሁ ቢላውን ይሞርድ እርዱንም ይገላግለው።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tagalog ئۇيغۇرچە Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ Русский Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip සිංහල دری Svenska Čeština Fulfulde ગુજરાતી Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių Malagasy Nederlands or Română Kinyarwanda Српски тоҷикӣ ไทย O‘zbek Yorùbá Moore नेपाली Oromoo Wolof Soomaali Български Українська Azərbaycan bm ქართული Македонскиالشرح
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ በኛ ላይ በሁሉም ነገሮችኢሕሳንን ግዴታ እንዳደረገ ተናገሩ። ማሳመር (ኢሕሳን) ማለት በአምልኮውም ውስጥ፣ መልካምን ሲፈፅምም፣ ከፍጡራን ላይ ጎጂን ነገር ሲያስወግድም ዘወትር አላህ ያየኛል ማለት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በመግደልና በማረድ ውስጥ ማሳመርም አንዱ ነው። በመግደል ኢሕሳን ሲባል በቂሷስ (ሸሪዐዊ የቅጣት ብይን ለምሳሌ የገደለ መገደል) ተፈፃሚነት ወቅት: ለመግደል ገሩን፣ ቀላሉንና የተገዳዩን ነፍስ በፍጥነት ሊያወጣ የሚችለውን መንገድ በመምረጥ ነው። በእርድ ማሳመር ሲባል ደግሞ እንስሳ በምናርድበት ወቅት ነው። ይህም መሳሪያውን በደንብ በመሞረድ ፣ የሚታረደው እንስሳ እያየ ፊት ለፊቱ ባለመሞረድና ሌላ እርዱን የሚመለከት እንስሳ ቦታው ላይ እያለ ባለማረድ ለእንስሳ በማዘን ነው።فوائد الحديث
የላቀውና የተከበረው አላህ በፍጡራኑ ላይ ያለው እዝነትና ርህራሄን፤
አገዳደልና አስተራረድ ላይ ኢሕሳን የሚባለው ሸሪዐውን የተከተለ (የዋጀ) በሆነ መልኩ ሲፈፀም ነው።
ሸሪዐ ምሉዕና ሁሉንም መልካም ነገር የጠቀለለ ሲሆን ከዚህም መካከል ለእንስሳት ማዘኑና መራራቱ አንዱ ነው፤
የሰውን ልጅ ከገደሉ በኋላ ሰውነቱን መቆራረጥ መከልከሉን፤
እንስሳትን መቅጣት ያለበት ነገር ሁሉ ክልክል መሆኑን ተረድተናል።