አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ንግግሮች አራት ናቸው። 'ሱብሓነላህ' (አላህ ሆይ! ጥራት ተገባህ) 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው።) 'ላኢላሃ ኢለላህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት…

አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ንግግሮች አራት ናቸው። 'ሱብሓነላህ' (አላህ ሆይ! ጥራት ተገባህ) 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው።) 'ላኢላሃ ኢለላህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) 'አሏሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) በማንኛቸውም ብትጀምር አይጎዳህም።

ከሰሙረህ ቢን ጁንዱብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "አላህ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ንግግሮች አራት ናቸው። 'ሱብሓነላህ' (አላህ ሆይ! ጥራት ተገባህ) 'አልሐምዱ ሊላህ' (ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው።) 'ላኢላሃ ኢለላህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) 'አሏሁ አክበር' (አላህ ታላቅ ነው።) በማንኛቸውም ብትጀምር አይጎዳህም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ ዘንድ ተወዳጅ ንግግሮች አራት መሆናቸውን ተናገሩ: "ሱብሓነላህ": ማለትም አላህን ከሁሉም ጉድለት ማጥራት ነው። "አልሐምዱ ሊላህ": አላህን ከመውደድና ከማላቅ ጋር በምሉዕነት ባህሪ መግለፅ ነው። "ላኢላሃ ኢለላህ": ማለትም ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። "አላሁ አክበር": ማለትም አላህ ከሁሉም ነገር የበለጠ ታላቅና ሀያል ነው። ትሩፋቷንና ምንዳዋን ለማግኘት የቃላቱን ቅደም ተከተል መጠበቅ ግዴታ አይደለም።

فوائد الحديث

በማንኛውም ቃል መጀመር ምንም ችግር አለማሳደሩ ሸሪዓ ገር መሆኑን ያስረዳናል።

التصنيفات

ልቅ የሆኑ ዚክሮች