إعدادات العرض
ሁለት ሙስሊሞች በሰይፋቸው (ሊጋደሉ) የተገናኙ ጊዜ ገዳዩም ሆነ ተገዳዩ እሳት ውስጥ ናቸው።
ሁለት ሙስሊሞች በሰይፋቸው (ሊጋደሉ) የተገናኙ ጊዜ ገዳዩም ሆነ ተገዳዩ እሳት ውስጥ ናቸው።
ከአቢ በክረህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ የአላህን መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ "ሁለት ሙስሊሞች በሰይፋቸው (ሊጋደሉ) የተገናኙ ጊዜ ገዳዩም ሆነ ተገዳዩ እሳት ውስጥ ናቸው። " እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህ ገዳይ ሆኖ (እሳት መግባቱ መልካም) ተገዳዩ (እሳት የሚገባው) በምን ጥፋቱ ነው?" አልኩ። እርሳቸውም "እሱ ባልደረባውን ለመግደል ጉጉ ስለነበር ነው።" አሉ።
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands සිංහල தமிழ் ไทย دری Fulfulde Magyar ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių or Română Kinyarwanda Српски тоҷикӣ O‘zbek Moore नेपाली Oromoo Wolof Soomaali Български Українська Azərbaycan bm ქართული Македонски Lingala Ελληνικά Akan kmالشرح
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁለት ሙስሊሞች እርስ በርሳቸው እያንዳንዳቸው የባልደረባውን ህይወት ማጥፋትን ቋምጠው በሰይፋቸው ሊጋደሉ የተገናኙ እንደሆነ ሁለቱም እሳት እንደሚገቡ ተናገሩ። ገዳዩ ባለደረባውን በመግደሉ ምክንያት እሳት ውስጥ ይገባል። ሰሐቦች የተገዳዩ እሳት መግባት ግራ አጋባቸው: እንዴት የእሳት ይሆናል? ብለው ጠየቁ። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባልደረባውን ለመግደል በመጓጓቱ ፤ በገዳዩ ከመቀደም በስተቀር ከመግደል ምንም የከለከለው ነገር ስለሌለ እሱም ጭምር የእሳት መሆኑን ተናገሩ።فوائد الحديث
ወንጀል ለመስራት በልቡ የቆረጠና መዳረሻዎቹን የፈፀመ ሰው ለቅጣት የተገባ መሆኑን እንረዳለን።
ሙስሊሞች እርስ በርስ በመጋደላቸው ዙሪያ ብርቱ ማስጠንቀቂያና የእሳት ዛቻም መምጣቱን እንረዳለን።
በሙስሊሞች መካከል የተፈጠረው መጋደል ትክክል በሆነ ጉዳይ ከሆነ ዛቻ ውስጥ አይካተትም። ለምሳሌ ከመሪ ትእዛዝ የወጡ ወሰን አላፊዎችና ሀገር የሚያበላሹን መዋጋትን ይመስል።
ከባድ ወንጀል የሰራ ሰው በመስራቱ ብቻ ከሀዲ አይሆንም። ምክንያቱም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሁለቱን እርስ በርስ የሚጋደሉትን ሙስሊሞች ብለው ጠርተዋቸዋልና።
ሁለት ሙስሊሞች በማንኛውም ለመግደል የሚያደርስ በሆነ መሳሪያ ሊጋደሉ ተገናኝተው አንዱ አንዱን ቢገድል ገዳዩም ተገዳዩም እሳት ውስጥ ናቸው። ሐዲሡ ውስጥ ሰይፍ መጠቀሱ ለምሳሌ ያክል ብቻ ነው።