ከመልካም ነገር አንዳችም አታሳንስ ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን እንኳ (እንዳታሳንስ)።

ከመልካም ነገር አንዳችም አታሳንስ ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን እንኳ (እንዳታሳንስ)።

ከአቡ ዘር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉኝ: "ከመልካም ነገር አንዳችም አታሳንስ ወንድምህን ፈታ ባለ ፊት ማግኘትንም ቢሆን እንኳ (እንዳታሳንስ)።"

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ትንሽም ብትሆን እንኳ መልካምን ከመፈፀም እንዳናሳንስ አነሳሱን። ከነዚህ መካከልም ከሙስሊም ጋር በሚገናኝ ወቅት በፈገግታ ፊትን መፍታት ይጠቀሳል። አንድ ሙስሊም ይህን በመፈፀሙ ምክንያት ሙስሊም ወንድሙን ማዝናናትና በውስጡ ደስታን መጨመር ስለሚያመጣ በዚህ ላይ ሊጓጓ ይገባል።

فوائد الحديث

በአማኞች መካከል መዋደድ፣ ሲገናኙ ፈገግ ማለትና ማበሰር ያለውን ትሩፋት ፤

ሸሪዓ ለሙስሊሞች በሚጠቅምና ህብረታቸውን አንድ በሚያደርግ ነገር ሁሉ መምጣቱ የዚህ ሸሪዓን ምሉዕነትና ጠቅላይነት ፤

ትንሽም ብትሆን እንኳ መልካም በመስራት ላይ መበረታታቱን ፤

በሙስሊሞች መካከል አንድነትን ስለሚያረጋግጥ በሙስሊሞች ላይ ደስታን መጨመር ተወዳጅ መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

ምስጉን ስነ-ምግባር