إعدادات العرض
ሀሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አሉ። እሳቸውም "ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው።
ሀሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አሉ። እሳቸውም "ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው።
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፡ "ሀሜት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" ሶሐቦችም "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" አሉ። እሳቸውም "ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው።" አሉ። "የምናገረው ነገር ወንድሜ ላይ ካለስ (ሀሜት ይባላልን?)" ተብለው ተጠየቁ። እሳቸውም "የምትናገረው ነገር እሱ ላይ ካለ በርግጥ አምተሀዋል። እሱ ላይ ከሌለ ደግሞ በርግጥም ቀጥፈህበታል።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands ئۇيغۇرچە සිංහල ไทย دری Fulfulde Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių or Română Kinyarwanda Српски O‘zbek Moore नेपाली тоҷикӣ Oromoo Wolof Soomaali Malagasy Български Українська Azərbaycan ქართული bm Lingala Македонскиالشرح
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተከለከለውን ሀሜት እውነታ : ሙስሊምን በሌለበት በሚጠላው ነገር ማውሳት መሆኑን አብራሩ። ይህም ተፈጥሯዊውም ሆነ ስነ ምግባሪያዊ ባህሪውን ቢያወሳ ተመሳሳይ ነው። እውሩ ፣ አጭበርባሪ ፣ ውሸታምና የመሳሰሉትን እሱ ላይ የሚገኙ የተወገዙ መገለጫዎችን በማውሳት ማማትን የመሳሰለው ነው። እሱ ላይ የሌሉ ባህሪያት ከሆኑ ግን የተወሱት ከሀሜትም የባሰ ነው። እሱም መቅጠፍ (ቡህታን) ነው የሚሆነው :- ማለትም በሰው ላይ የሌሉበትን ባህሪያት መቅጠፍ ነው።فوائد الحديث
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እውቀትን ጥያቄያዊ በሆነ መንገድ ማስተላለፋቸውን ስናይ የሳቸው የማስተማር ስልት ውብ መሆኑን እንረዳለን ፤
ሶሐቦች "አላህና መልክተኛው ያውቃሉ።" ማለታቸውን ስናይ ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር ያላቸው አደብ ውብ መሆኑን እንረዳለን ፤
ተጠያቂ ስለማያውቀው ነገር "አላህ ያውቃል።" ማለት እንዳለበት እንረዳለን ፤
ሸሪዐ ሐቆችን በመጠበቅና በማህበረሰቡ መካከል ወንድማማችነትን በመፍጠር ማህበረሰቡን መጠበቁን እንረዳለን ፤
ሀሜት እንደአስፈላጊነቱ በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ካልሆነ በስተቀር ክልክል ነው። ከነዚህም ውስጥ: - በደልን ለመከላከል : ይህም "እከሌ በድሎኛል ወይም በኔ ላይ እንዲህ ፈፅሟል።" በማለት ተበዳይ ሀቁን ማስመለስ የሚችል ሰው ዘንድ የበደለውን በማውሳት ነው። በትዳር ጉዳይ ወይም በሽርክና ወይም በጉርብትናና በመሳሰሉት ጉዳይ ለማማከር ሰውዬውን ማማት ከሚፈቀዱት መካከል የሚመደብ ነው።
التصنيفات
የመናገርና የዝምታ ስነ-ስርዓት