إعدادات العرض
በአላህ ገንዘብ ያለአግባብ የሚገለገሉ ሰዎች ለነርሱ የትንሳኤ ቀን እሳት ተዘጋጅቶላቸዋል።
በአላህ ገንዘብ ያለአግባብ የሚገለገሉ ሰዎች ለነርሱ የትንሳኤ ቀን እሳት ተዘጋጅቶላቸዋል።
ከኸውለህ አልአንሷሪይ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "በአላህ ገንዘብ ያለአግባብ የሚገለገሉ ሰዎች ለነርሱ የትንሳኤ ቀን እሳት ተዘጋጅቶላቸዋል።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ Deutsch 日本語 پښتو Tiếng Việt অসমীয়া Shqip Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá Nederlands සිංහල Hausa ไทย دری Fulfulde Magyar Italiano ಕನ್ನಡ Кыргызча Lietuvių or Română Kinyarwanda Српски O‘zbek Moore नेपाली Oromoo Wolof Soomaali Malagasy Български Українська Azərbaycan ქართული Lingala bm тоҷикӣ Македонскиالشرح
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሙስሊሞችን ገንዘብ ያለአግባብ ስለሚጠቀሙና ያለአግባብ ስለሚበዘብዙ ሰዎች ተናገሩ። ይህም ገንዘብን ባልተፈቀደ መልኩ ማጠራቀምና ማግኘትን እንዲሁም ትክክለኛ ባልሆነ ቦታ ፈሰስ ማድረግን የሚጠቀልል ሀሳብ ነው። የየቲሞችን ገንዘብ መብላት፣ ወቅፍ የተደረገን ገንዘብ መብላት፣ አደራዎችን መካድ፣ የማህበረሰቡን ገንዘብ ያለአግባብ መውሰድ ሁሉ እዚህ ውስጥ ይካተታል። ቀጥለውም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የትንሳኤ ቀን የነዚህ ሰዎች ምንዳ እሳት መሆኑን ተናገሩ።فوائد الحديث
በሰዎች እጅ ያሉ ገንዘቦች እሱ በደነገገላቸው መንገድ እንዲያወጡትና ያለአግባብ ከመገልገል ይርቁ ዘንድ ሰዎችን ምትክ ያደረገበት የአሏህ ገንዘቡ ነው። ይህም መሪዎችንም ሆነ ሌሎችንም አጠቃላይ ሰዎችን የሚጠቀልል ነው።
ሸሪዓ በማህበረሰቡ ገንዘብ ዙሪያ ጥብቅ መሆኑን እንረዳለን። ከገንዘብ በጥቂቱም ቢሆን የተሾመ ሰው የትንሳኤ ቀን ስለገንዘቡ አሰባሰብም ሆነ ስለአወጣጡ ይተሳሰባል።
የራሱንም ገንዘብ ሆነ የሌላውን ገንዘብ ሸሪዓዊ ባልሆነ መልኩ የሚገለገልም በዚህ ዛቻ ይካተታል።