إعدادات العرض
የቀጭን ሐርንና የወፍራም ሐርን ልብስ አትልበሱ! በወርቅና ብር እቃ አትጠጡ! በ(ወርቅና ብር) ትሪም አትብሉ! እርሷ በዚህ ዓለም ለነርሱ ናት፤ በመጪው ዓለም ደግሞ ለኛ ናት።
የቀጭን ሐርንና የወፍራም ሐርን ልብስ አትልበሱ! በወርቅና ብር እቃ አትጠጡ! በ(ወርቅና ብር) ትሪም አትብሉ! እርሷ በዚህ ዓለም ለነርሱ ናት፤ በመጪው ዓለም ደግሞ ለኛ ናት።
ከዐብዱረሕማን ቢን አቢ ለይላ እንደተላለፈው እነርሱ ሑዘይፋ ዘንድ ነበሩ። የሚጠጣ እንዲሰጡት ሲጠይቅ አንድ እሳት አምላኪ የሚጠጣ (በብር እቃ) ሰጠው። እቃውን (በሑዘይፋ) እጁ ላይ ሲያኖረውም በርሱ ወረወረበትና እንዲህ አለ: "ከአንድና ሁለት ጊዜ በላይ ባልከለክለው ኖር ‐ ይህን አላደርግም ነበር ‐ ነበር። ነገር ግን ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ: "የቀጭን ሐርንና የወፍራም ሐርን ልብስ አትልበሱ! በወርቅና ብር እቃ አትጠጡ! በ(ወርቅና ብር) ትሪም አትብሉ! እርሷ በዚህ ዓለም ለነርሱ ናት፤ በመጪው ዓለም ደግሞ ለኛ ናት።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî മലയാളം Kiswahili සිංහල دری Svenska অসমীয়া ไทย Tiếng Việt Yorùbá Кыргызча ગુજરાતી Malagasy नेपाली Română Nederlands Soomaali Oromoo پښتو తెలుగు Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Српски Mooreالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የሐርን ልብስ በየትኛውም አይነቱ ከመልበስ ወንዶችን ከለከሉ። ወንዶችንም ሴቶችንም በወርቅና ብር እቃዎችና መሳሪያ ከመብላትና ከመጠጣት ከለከሉ። ይህም አማኞች በዚህች አለም አላህን ለመታዘዝ እንደራቁት ሁሉ የትንሳኤ ቀን ደግሞ ለአማኞች ብቻ እንደሆነ ተናገሩ። ከነዚህ መካከልም ለከሀዲያኖች በመጪው ዓለም ምንም የላቸውም። ምክንያቱም የአላህን ትእዛዝ በማመፅ ቸኩለው በዚህ ዓለም ህይወታቸው ምርጥ የሚሉትን ነገሮች በመያዝ ስለተጠቀሙ ነው።فوائد الحديث
በወንዶች ላይ ቀጭንና ወፍራም ሐር ክልክል መሆኑንና የለበሰው ላይም ብርቱ ዛቻ እንዳለበት እንረዳለን።
ቀጭንና ወፍራም ሐር መልበስ ለሴቶች ይፈቀዳል።
በወንድም ሆነ በሴቶች ላይ በወርቅና ብር ትሪዎችና እቃዎች መብላትና መጠጣት ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
የሑዘይፋ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና አወጋገዝ ጠንከር ያለ መሆኑን እንመለከታለን። የዚህንም ምክንያት ከአንድ ጊዜ በላይ የወርቅና ብር እቃዎችን እንዳይጠቀም መከልከሉና እርሱ ግን አለመቆጠቡ እንደሆነ ገልጿል።
التصنيفات
የአለባበስ ስነ-ስርዓት