إعدادات العرض
የእውነት ሰማእትነትን እንዲሰጠው አላህን የጠየቀ ሰው ፍራሹ ላይ ቢሞት እንኳ አላህ የሰማእታትን ደረጃ ያደርሰዋል።
የእውነት ሰማእትነትን እንዲሰጠው አላህን የጠየቀ ሰው ፍራሹ ላይ ቢሞት እንኳ አላህ የሰማእታትን ደረጃ ያደርሰዋል።
ከሰህል ቢን ሑነይፍ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "የእውነት ሰማእትነትን እንዲሰጠው አላህን የጠየቀ ሰው ፍራሹ ላይ ቢሞት እንኳ አላህ የሰማእታትን ደረጃ ያደርሰዋል።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Kiswahili Português සිංහල অসমীয়া ગુજરાતી Tiếng Việt Nederlands پښتو नेपाली ไทย Svenska മലയാളം Кыргызча Română తెలుగు Malagasy ಕನ್ನಡالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአላህ መንገድ ሰማእት መሆንንና መገደልን የፈለገ፣ በዚህ ፍላጎቱም ለአላህ አጥርቶና እውነተኛ ሆኖ ከሆነ የጠየቀው ጂሀድ ሳያደርግ ፍራሽ ላይ ቢሞት እንኳ አላህ በእውነተኛ ኒያው የሰማእታትን ደረጃ እንደሚሰጠው ተናገሩ።فوائد الحديث
የተፈለገውን ሥራ ባይሰራ እንኳ የሚቻለውን ከመስራት ጋር እውነተኛ ኒያ መነየት የተፈለገው ምንዳና አጅር ላይ ለመድረስ ሰበብ እንደሚሆነው እንረዳለን።
ጂሀድ ማድረግና በአላህ መንገድ ሰማእት መሆን በመፈለግ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
አላህ ይህን ኡማ ማላቁን እንረዳለን። ይህ ኡማ በትንሽ ስራ ጀነት ውስጥ ከፍተኛ ደረጃን እንዲያገኝ ታድሏልና።