إعدادات العرض
ሲሸጥም፣ ሲገዛም ይሁን ያበደረውን ሲያስመልስ ገር የሆነን ሰው አሏህ ይዘንለት።
ሲሸጥም፣ ሲገዛም ይሁን ያበደረውን ሲያስመልስ ገር የሆነን ሰው አሏህ ይዘንለት።
ከጃቢር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንደተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፡ "ሲሸጥም፣ ሲገዛም ይሁን ያበደረውን ሲያስመልስ ገር የሆነን ሰው አሏህ ይዘንለት።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]
الترجمة
ar bn bs en es fa fr id ru tl tr ur zh hi si ug ku ha pt ml te my de ja ps vi as sq sv cs gu yo nl sw ta prs bg ff hu kn ky lt or ro rw tg uz ak ne mos az wo om so uk km bm rn ka mk sr el mgالشرح
ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲሸጥ ለስላሳ፣ ቸርና ለጋስ ለሆነ ሁሉ የአሏህን እዝነት እንዲያገኝ ዱዓእ አደረጉለት፤ ይህም ዋጋውን በማናር ገዥን አያጨናንቅም፤ ይልቁን በመልካም ምግባር ይዋዋለዋል። ሲገዛም ለስላሳ፣ ቸርና ለጋስ ስለሆነ እቃውን በማሳነስና በማጣጣል ዋጋውን አያራክስም። ያበደረውን እዳ ሲያስመልስም ለስላሳ፣ ቸርና ለጋስ ስለሆነ ገንዘቡ እጅግ ያስፈለገውን ድሀ አያካብድበትም፤ ይልቁንም በእዝነትና ርህራሄ ይጠይቃል፤ ለተጨናነቀም የጊዜ ፋታ ይሰጣል።فوائد الحديث
በሰዎች መካከል ያለን መስተጋብር ማስተካከል ሸሪዓው ከሚፈልጋቸው ዋንኛ ተፈላጊ ጉዳዮች መካከል መሆኑን እንረዳለን።
በሽያጭና በግዥም ይሁን በሌላም መስክ ከሰዎች ጋር ባለን መስተጋብር እጅግ ያማረውን ስነምግባር መላበስ የሚበረታታ መሆኑን እንረዳለን።
التصنيفات
ምስጉን ስነ-ምግባር