ጀነት ወደ እያንዳንዳችሁ ከጫማው ማሰሪያ የበለጠ ቅርብ ናት። እሳትም እንደዚሁ።

ጀነት ወደ እያንዳንዳችሁ ከጫማው ማሰሪያ የበለጠ ቅርብ ናት። እሳትም እንደዚሁ።

ኢብኑ መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ማለቱ ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡ "ጀነት ወደ እያንዳንዳችሁ ከጫማው ማሰሪያ የበለጠ ቅርብ ናት። እሳትም እንደዚሁ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለሰው ልጅ ጀነትም ይሁን ጀሀነም በእግሩ ላይ እንዳለው የጫማው ማሰሪያ ቅርብ መሆናቸውን ተናገሩ። ምክንያቱም (ሳያስበው) አሏህን የሚያስደስት የሆነን መልካም ስራ ይሰራና በዛ ሰበብ ጀነት ይገባል። ወይም መጥፎ ስራ ይሰራና ጀሀነም ለመግባት ሰበብ ይሆንበታል።

فوائد الحديث

ትንሽ ቢሆንም መልካም ስራ ላይ መበርታት፤ ትንሽ ቢሆንም ከክፋት መጠንቀቅ እንደሚገባ፤

ሙስሊም በህይወቱ በራሱ ሁኔታ ሳይሸወድ ሁሌም በተስፋና በስጋት መካከል ሊሆን እና እውነት ላይ እንዲያፀናውም ጥራት የተገባው አሏህን ሊማፀን የግድ እንደሚገባው እንረዳለን።

التصنيفات

የጀነትና እሳት ባህሪዎች