አደራችሁን ጥርጣሬን ተጠንቀቁ! ጥርጣሬ እጅግ ውሸት የሆነ ወሬ ነውና።

አደራችሁን ጥርጣሬን ተጠንቀቁ! ጥርጣሬ እጅግ ውሸት የሆነ ወሬ ነውና።

አቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ማለታቸውን አስተላልፈዋል: "አደራችሁን ጥርጣሬን ተጠንቀቁ! ጥርጣሬ እጅግ ውሸት የሆነ ወሬ ነውና። አትፈላፈሉ፣ አትሰልሉ፣ አትመቀኛኙ፣ ጀርባም አትሰጣጡ፣ አትጠላሉ (ይልቁንም) ወንድማማች የአላህ ባሮች ሁኑ።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሙስሊሞች መካከል ወደ ክፍፍልና ጠላትነት ከሚያደርሱ አንዳንድ ነገሮች ከለከሉን፤ አስጠነቀቁንም። ከነዚህም መካከል: (ጥርጣሬ) ያለማስረጃ በቀልብ ውስጥ የሚወድቅ መጥፎ እሳቤ ነው። ከወሬዎች ሁሉ እጅግ ውሸት መሆኑን ገለፁ። (መፈላፈል): ይህም በአይን ወይም በጆሮ የሰዎችን ነውር መፈለግ ነው። (መሰለል): ይህም ማለት ድብቅ የሆኑ ነገሮችን መፈለግ ነው። በብዛት ይህ ቃል የሚውለው የሰዎችን መጥፎ ነገር መፈለግን ለማመልከት ነው። (ምቀኝነት): ይህም ማለት ሌሎች ፀጋ ማግኘታቸውን መጥላት ማለት ነው። (ጀርባ መሰጣጠት) : ለሙስሊም ወንድሙ ሰላምታን ላይሰጥና ላይዘይር ከፊሉ ከከፊሉ መዞሩ ነው። (መጠላላት) : ሌሎችን በማስቸገር፣ ፊትን በማጨፍገግና በመጥፎ መስተጋብር በመሳሰሉት ሰዎችን መጥላትና ማሸሽ ነው። ቀጥለውም ሙስሊሞች የእርስ በርስ ሁኔታቸው የሚስተካከሉበትን ጠቅላይ ንግግር እንዲህ በማለት ተናገሩ "ወንድማማች የአሏህ ባሮች ሁኑ።" ወንድማማችነት በሰዎች መካከል ያለውን ግንኙነት የሚሰበስብ፣ በመካከላቸው መዋደድንና ቅርርብን የሚጨምር ማሰሪያ ገመድ ነው።

فوائد الحديث

በመጥፎ የሚያስጠረጥር ምልክት ግልፅ የሆነበትን ሰው መጠራጠር ምንም አይጎዳም። አማኝ የሆነ ሰውም በመጥፎዎችና አመፀኞች እንዳይሸወድ ብልጥና ጮሌ መሆን ይገባዋል።

በሐዲሱ የተፈለገው ነፍስ ውስጥ ፀንቶ በሚቆይ መልኩ (በጥርጣሬ) መወንጀል እና በጥርጣሬም ላይ ከመዘውተር ማስጠንቀቅ ነው። ነፍስ ላይ ባልፀና መልኩ መጠርጠር ከሆነ ግን ይህ ተጠያቂ አያደርግም።

በሙስሊሙ ማህበረሰብ ውስጥ በሚገኙ ግለሰቦች መካከል ለመናቆርና ለመቆራረጥ ምክንያት የሚሆኑ እንደ መሰለል፣ መመቅኘትና የመሳሰሉት ነገሮች መከልከላቸውን እንረዳለን።

በተቆርቋሪነትና በመዋደድ ረገድ ከሙስሊም ጋር ሊኖረን የሚገባው መስተጋብር ወንድማዊ መስተጋብር መሆን እንዳለበት መታዘዛችንን እንረዳለን።

التصنيفات

ውግዝ ስነ-ምግባር