ለሰዎች የማይራራን አሸናፊና የበላይ የሆነው አላህ አይራራለትም።

ለሰዎች የማይራራን አሸናፊና የበላይ የሆነው አላህ አይራራለትም።

ከጀሪር ቢን ዐብደላህ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ለሰዎች የማይራራን አሸናፊና የበላይ የሆነው አላህ አይራራለትም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለሰዎች የማይራራ ሰውን የላቀውና የተከበረው አላህም እንደማይራራለት ገለፁ። ሰው ለፍጡር ማዘኑ የአላህን ርህራሄ ማግኛ ከሆኑ ትላልቅ ሰበቦች መካከል ነው።

فوائد الحديث

ርህራሄ ለሌሎቹም ፍጡራን ያስፈልጋል። ነገር ግን ሀዲሱ ላይ ሰውን ብቻ የጠቀሰው አፅንኦት ለመስጠት ነው።

አላህ ለአዛኝ ባሮቹ የሚራራ አዛኝ ጌታ ነው። ምንዳ በስራ አይነት ነው።

ለሰው ማዘን ሲባል ለነሱ መልካም ማድረግን፣ ጉዳትን ከነርሱ ላይ መከላከልንና ባማረ መልኩ ከነርሱ ጋር መኗኗርን ይጠቀልላል።

التصنيفات

ምስጉን ስነ-ምግባር