إعدادات العرض
ዱንያ ጣፋጭና አረንጓዴ (ለምለም) ናት። አላህም እንዴት እንደምትሰሩ ሊያያችሁ በውስጧ ምትኮች አድርጓችኋል። ዱንያንም ተጠንቀቁ! ሴቶችንም ተጠንቀቁ!
ዱንያ ጣፋጭና አረንጓዴ (ለምለም) ናት። አላህም እንዴት እንደምትሰሩ ሊያያችሁ በውስጧ ምትኮች አድርጓችኋል። ዱንያንም ተጠንቀቁ! ሴቶችንም ተጠንቀቁ!
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦ "ዱንያ ጣፋጭና አረንጓዴ (ለምለም) ናት። አላህም እንዴት እንደምትሰሩ ሊያያችሁ በውስጧ ምትኮች አድርጓችኋል። ዱንያንም ተጠንቀቁ! ሴቶችንም ተጠንቀቁ! የበኒ ኢስራኢሎች የመጀመሪያ ፈተና የተከሰተው በሴቶች ነበርና።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt Hausa Kurdî Kiswahili Português සිංහල Svenska Čeština ગુજરાતી Yorùbá ئۇيغۇرچە ไทย پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or नेपाली Malagasy Kinyarwanda Română తెలుగు Lietuvių Oromoo മലയാളം Nederlands Soomaali Shqip Српски Deutsch Українська ಕನ್ನಡ Wolof Mooreالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዱንያ ስትቀመስ ጣፋጭ ስትታይ ደግሞ አረንጓዴ ለምለም ስለሆነች ሰው በርሷ እንደሚሸወድ፣ በርሷ እንደሚሰምጥና ትልቁ ጉዳዩ እንደሚያደርጋትም ገለፁ። ከፍ ያለውና ጥራት የተገባው አላህ በዚህች የዱንያ ህይወት እንዴት እንደምንሰራና ለርሱ ታዛዥ እንሆናለን? ወይስ እናምፀዋለን? የሚለውን ለመመልከት ከፊላችን ከፊሉን እንዲተካ አድርጓል። ከዚያም: "የዱንያ መጣቀሚያና ጌጧ እንዳይሸውዳችሁ፤ አላህ ያዘዛችሁን ለመተውና በከለከላችሁ ላይ ለመውደቅ እንዳያነሳሳችሁ ተጠንቀቁ! አሉ። እጅግ ትልቁ ከዱንያ ፈተናዎች መካከል መጠንቀቅ ግድ የሚሆንብንም የሴቶች ፈተና ነው። ሴት በኒ ኢስራኢሎች የወደቁበት የመጀመሪያዋ ፈተና ናት።"فوائد الحديث
ጥንቁቅነትን አጥብቆ በመያዝ ላይና በዱንያ ውጫዊ ገፅታና ጌጧ አለመሸወድ ላይ መነሳሳቱ።
ሴቶችን በማየት ወይም ከባዕድ ወንዶች ጋር መቀላቀላቸውን በማቃለል ወይም ከዚህ ውጪም ባሉ መፈተኛዎች በሴቶች ፈተና ከመውደቅ መጠንቀቅ እንደሚገባ እንረዳለን።
የሴቶች ፈተና ከዱንያ እጅግ ትላልቅ ፈተናዎች መካከል አንዱ ነው።
ባለፉት ህዝቦች መገሰፅና ትምህርትን መውሰድ እንደሚገባ እንረዳለን። በኒ ኢስራኢሎች ላይ የተከሰተው ሌላውም ላይ ሊከሰት ይችላልና።
የሴቶች ፈተና ሲባል ሚስት ከሆነች ሰውየውን ከአቅሙ በላይ በሆነ ወጪ ታስገድደውና በዚህም ዲናዊ ጉዳዮችን ከመፈለግ ጠምዳው ሙሉ ጊዜውን ዱንያን በመፈለግ ላይ እያዋለ እንዲጠፋ ታደርገዋለች፤ ባዕድ ሴት ከሆነች ደግሞ የርሷ ፈተና ከቤቷ በምትወጣ ወቅትና ከወንዶች ጋር በምትቀላቀል ጊዜ ወንዶችን ማታለሏና ከእውነት ዞር እንዲሉ ማድረጓ ነው። በተለይ ደግሞ የተራቆቱና የተገላለጡ ከሆኑ እንደየደረጃው ዝሙት ላይ ወደ ለመውደቅ ይዳርጓቸዋል። ስለዚህም የትኛውም አማኝ በአላህ ለመጠበቅና ከነርሱ ፈተና ለመዳን ከአላህ ጋር ትስስሩን ማጠንከር ይገባዋል።