አትቆጣ!

አትቆጣ!

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተዘገበው እንዲህ አሉ: አንድ ሰውዬ ለነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አለ: "ምከሩኝ!" እሳቸውም "አትቆጣ!" አሉት። ጥያቄውን ደጋግሞ መላልሶ ጠየቃቸው እርሳቸውም "አትቆጣ!" አሉት።

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ከሰሓቦች አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና አንዱ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ የሚጠቅመውን ነገር እንዲጠቁሙት ፈለገ። እርሳቸውም እንዳይቆጣ አዘዙት። ይህም ማለት ወደቁጣ የሚያነሳሱ ምክንያቶችን እንዲርቅ፣ የሚያስቆጣ ነገር በተከሰተ ጊዜም ነፍሱን እንዲቆጣጠር፣ በቁጣው ወደ መግደል፣ መማታት፣ ስድብና የመሳሰሉት ነገር እንዳይሻገር ማለት ነው። ሰውዬውም በተደጋጋሚ ምክር እንዲጨምሩለት ፈለገ። ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "አትቆጣ!" ከምትለው ምክር የዘለለ ምንም አልጨመሩለትም።

فوائد الحديث

ከቁጣና መንስኤዎቹ መጠንቀቅ እንደሚገባ፤ ቁጣ የክፋት መሰብሰቢያ ነው። ከሱ መጠበቅ የመልካም መሰብሰቢያ ነው።

ለአላህ ብሎ መቆጣት የአላህ ክልከላዎች ሲደፈሩ መቆጣትን ይመስል ምስጉን የሆነ ቁጣ ነው።

ሰሚው እስኪሸመድደውና አንገብጋቢነቱን እስኪገነዘብ ድረስ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ንግግርን መደጋገም እንደሚገባ፤

አዋቂ ከሆነ ሰው ምክር መፈለግ ያለውን ትሩፋት ተረድተናል።

التصنيفات

ምስጉን ስነ-ምግባር