إعدادات العرض
የትንሳኤ ቀን ከመልካም ስነ ምግባር የበለጠ የአማኝን ሚዛን የሚደፋ አንድም ነገር የለም። አላህ ፀያፍ የሚሰራንና ፀያፍ የሚናገርን ይጠላል።
የትንሳኤ ቀን ከመልካም ስነ ምግባር የበለጠ የአማኝን ሚዛን የሚደፋ አንድም ነገር የለም። አላህ ፀያፍ የሚሰራንና ፀያፍ የሚናገርን ይጠላል።
ከአቡ ደርዳእ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ: "የትንሳኤ ቀን ከመልካም ስነ ምግባር የበለጠ የአማኝን ሚዛን የሚደፋ አንድም ነገር የለም። አላህ ፀያፍ የሚሰራንና ፀያፍ የሚናገርን ይጠላል።"
[ሶሒሕ ነው።] [አቡዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Português සිංහල Svenska ગુજરાતી Yorùbá ئۇيغۇرچە Tiếng Việt Kiswahili پښتو অসমীয়া دری Кыргызча or Malagasy नेपाली Čeština Oromoo Română Nederlands Soomaali తెలుగు മലയാളം ไทย Српски Kinyarwanda ಕನ್ನಡ Lietuvių Wolof Українська ქართული Moore Magyar Shqipالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የትንሳኤ ቀን ከተግባሮችም ከንግግሮችም የአማኝን ሚዛን የሚደፋለት መልካም ስነ ምግባር መሆኑን ተናገሩ። ይህም ፊትን ፈታ በማድረግ፣ ሌላን ከመጉዳት በመቆጠብና መልካም ነገርን ለሌሎች በመለገስ ነው። የላቀው አላህ፤ በድርጊትም ይሁን በንግግር አፀያፊ የሆነንም በአንደበቱ ብልግና የሚናገርንም ሰው ይጠላል።فوائد الحديث
የመልካም ስነ ምግባርን ትሩፋት እንረዳለን። መልካም ስነምግባር ባለቤቱን የአላህን ውዴታና የባሮቹን ውዴታ እንዲያገኝ ያበቃዋል። እርሱ የትንሳኤ ቀን ከሚመዘኑትም እጅግ ትልቁ ነው።