አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።

አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለነፍሱ የሚወደውን አምልኮዎችና ሃይማኖታዊም ይሁን ዱንያዊ መልካም ነገሮችን ለወንድሙ እስከሚወድ ድረስ፤ ለነፍሱ የሚጠላውንም ለርሱም እስኪጠላ ድረስ ለአንድ ሙስሊም የተሟላ ኢማን እንደማይረጋገጥ ገለፁ። በሙስሊም ወንድሙ ላይ የዲን ጉድለት ከተመለከተም ለማስተካከል ይታገላል። በርሱ ላይ መልካምን ከተመለከተም ያበረታዋል፣ ያግዘዋል፣ የዲኑን ወይም የዱንያውን ጉዳይም ይመክረዋል።

فوائد الحديث

አንድ ሙስሊም ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ የመውደድ ግዴታ እንዳለበት እንረዳለን። ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ የማይወድ ሰው ላይ ኢማን ውድቅ መደረጉ ይህን መተግበር ግዴታ መሆኑን ይጠቁማልና።

ለአላህ ብሎ ወንድማማች መሆን ከዘር ወንድማማችነትም በላይ ነው። የኢስላማዊ ወንድማማችነት ግዴታውም የበለጠ ነው።

ይህንን ውዴታ የሚቃረን ሁሉ ማጭበርበር፣ ሀሜት፣ ምቀኝነት፣ በሙስሊም ነፍስ ላይ ወይም ገንዘቡ ላይ ወይም ክብሩ ላይ ጠላት መሆንን የመሳሰሉ ንግግርም ሆነ ተግባርም ክልክል መሆኑን እንረዳለን።

"ለወንድሙ" ከሚለው ቃል ለአንድ ተግባር የሚያነሳሳ የሆነን ቃል መጠቀም እንደሚገባ እንረዳለን።

ኪርማኒ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል: «ከዚህም በተጨማሪ ለነፍሱ የሚጠላውን መጥፎ ነገር ለወንድሙ መጥላቱም የኢማን ክፍል ነው። ሐዲሡ ላይ ያልጠቀሱት አንድን ነገር መውደድ ተቃራኒውን መጥላት የሚያስፈርድ ስለሆነ በዚህ በመብቃቃት መጥቀሱን ተዉት።

التصنيفات

ምስጉን ስነ-ምግባር