إعدادات العرض
በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውንም የጠላኸው ነገር ነው።
በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውንም የጠላኸው ነገር ነው።
ከነዋስ ቢን ሰምዓን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው: ነቢዩ - የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ «" በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውንም የጠላኸው ነገር ነው።» «ከዋቢሳህ ቢን መዕበድ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድ መጣሁ። እርሳቸውም: "የመጣኸው ስለበጎ ተግባርና ወንጀል ልትጠይቅ ነውን?" አሉኝ። እኔም: "አዎን" አልኳቸው። እርሳቸውም: "ነፍስህን ፈትሻት! በጎ ተግባር ነፍስ በርሱ የረጋችበት፣ ቀልብ በርሱ የሰከነችበት ነው። ወንጀል ደግሞ ሰዎችን ፈትዋ ጠይቀህ ፈትዋ ቢሰጡህ እንኳ ነፍስህ ውስጥና ደረትህ ውስጥ የተመላለሰ ነው።" አሉኝ።»
الترجمة
العربية Español English اردو Indonesia বাংলা Français Türkçe Русский Bosanski සිංහල हिन्दी 中文 فارسی Tiếng Việt Tagalog Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் ไทย Deutsch پښتو অসমীয়া Shqip Nederlands ગુજરાતી Кыргызча नेपाली Lietuvių دری Српски тоҷикӣ Kinyarwanda Magyar Čeština Moore Malagasy Oromoo ಕನ್ನಡ Wolof Azərbaycan O‘zbek Українська ქართული Македонски ភាសាខ្មែរ ਪੰਜਾਬੀ मराठी Kirundi Kurmancî Bahasa Melayuالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ስለበጎ ተግባርና ወንጀል ተናገሩ። እንዲህም አሉ: የበጎ ተግባር ትልቁ ነገር ከአላህ ጋር እርሱን በመፍራት፤ ከፍጡራን ጋር ደግሞ የሚያደርሱብንን አዛ (ችግር) በመቻል፣ ቁጣን በመቀነስ፣ ፊትን በመፍታት፣ ንግግርን በማሳመር፣ ዝምድናን በመቀጠል፣ በመታዘዝ፣ በመራራት፣ በጎ በመስራት፣ መልካም ቤተሰብና ባልደረባ በመሆን መልካም ስነምግባርን መላበስ ነው። በጎ ተግባር ማለት ልብና ነፍስ የረጋበትና የሰከነበት ነገር ነው። ወንጀል ማለት ደግሞ ልብህ ለርሱ ሳይከፈት ነፍስህ ውስጥ የተመላለሰ፣ የከነከነህ አሻሚ ነገር ነው። ስትሰራው ወንጀል ይሆን እያልክ ቀልብህ ውስጥ ጥርጣሬ የሚከሰትበትና የምትፈራው፣ ፀያፍ ስለሆነም አርአያ የሚሆኑ፣ ታላላቅና የተሟላ ስብዕና ያላቸው ሰዎች ፊት ጉዳዩ እንዲታወቅብህ የማትፈልገው ጉዳይህ ነው። ይህም ነፍስ በተፈጥሮዋ ሰዎች መልካም ስራዋን እንዲያውቁላት ነው የምትፈልገው። አንዳንድ ስራዋ ይፋ መውጣቱን ከጠላች ግን ያ ስራ ወንጀል ነውና ምንም መልካም የለውም። በነፍስህ ውስጥ ይህ የብዥታ ምልክት እስካለና በነፍስህ ውስጥ እስከተመላለሰ ድረስ ሰዎች ፈትዋ ቢሰጡህ እንኳ የነርሱን ፈትዋ እንዳትወስድ! ምናልባት ፈትዋ ሰጪው ያለእውቀት ፈትዋ ሰጥቶበት ሊሆን ስለሚችል የጉዳዩ ብዥታነት ትክክለኛ እስከሆነ ድረስ ፈትዋው ብዥታውን የማስወገድ አቅም የለውም። ነገር ግን ፈትዋው የተሰጠው በትክክል የሸሪዓ ማስረጃ ላይ ተመስርቶ ከሆነ ፈትዋ ጠያቂው ልቡ ለመልሱ ክፍት ባይሆንም እንኳ የግዴታ ወደ ፈትዋው ሃሳብ መመለስ ግዴታ ነው።فوائد الحديث
በመልካም ስነምግባር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። መልካም ስነምግባር ከትላልቅ የበጎ ተግባር ጉዳዮች መካከል አንዱ ነውና።
እውነትና ጥመት በአማኝ ላይ ምንም አሻሚ አይሆኑበትም። ይልቁንም ልቡ ውስጥ ባለ ብርሃን አማካኝነት እውነትንም ያውቀዋል፤ ከጥመትም ይሸሻል ያወግዛል።
ከወንጀል ምልክቶች መካከል የልብ መከንከንና መመላለስ፣ ሰዎች ማወቃቸውንም መጥላትህ ነው።
ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ የሚያጠነጥነው ሰዎች ከሁለት ነገሮች አንዱን ትክክል ለይተው የማያቁት በሆነ አሻሚ ጉዳይ ላይ ነው። ያለበለዚያማ በሸሪዓ ትእዛዝ መጥቶበት ከዚህ በጎ ተግባር የሚቃረን በዛ ጉዳይ ሌላ ማስረጃ ግልፅ ካልሆነለት፤ ልክ እንደዚሁ በተከለከሉ ወንጀሎች ዙሪያም በተቃራኒ ክልክልነቱን የሚቃረን ማስረጃ ከሌለ በነዚህ ጉዳይ ቀልብን መጠየቅና መረጋጋቷን ማጣራት ምንም አያስፈልግም።"
ሐዲሡ የሚመለከተው የንፁህ ተፈጥሮ ባለቤቶችን ነው እንጂ ከስሜቱ ጋር የተጣጣመውን ካልሆነ በቀር መልካምን በመልካምነቱ መጥፎን በመጥፎነቱ የማያውቅ የተቀለበሰ ቀልብ ባለቤትን አይመለከተውም።
ጢቢይ እንዲህ ብለዋል: "በተለያዩ ሐዲሦች በጎ ተግባር በብዙ ትርጉሞች ተተርጉሟል። አንድ ቦታ ላይ ነፍስ ወደርሱ የተረጋጋችበት፣ ቀልብም ወደርሱ የሰከነችበት ብለው ተርጉመውታል፤ አንድ ቦታ ላይ ደግሞ በኢማን ተርጉመውታል፤ በአንድ ቦታ ላይ ደግሞ ወደ አላህ የሚያቀርብክ ነገር ብለው ተርጉመውታል፤ እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ደግሞ በመልካም ስነምግባር ተርጉመውታል። መልካም ስነምግባርም: ጉዳትን በመቻል፣ ቁጣን በመቀነስ፣ ፊትን በመፍታት፣ ንግግርን በማሳመር ተተርጉሟል። ሁሉም ትርጓሜ ሀሳባቸው ተመሳሳይ ነው።"
