إعدادات العرض
አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።
አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።
የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አገልጋይ ከነበረው ከአቡ ሐምዛ አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም።"
الترجمة
العربية Español English اردو Indonesia বাংলা Français Türkçe Русский Bosanski සිංහල हिन्दी 中文 فارسی Tiếng Việt Tagalog Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ ไทย Deutsch 日本語 پښتو অসমীয়া Shqip Svenska Nederlands ગુજરાતી Кыргызча नेपाली Lietuvių دری Српски тоҷикӣ Kinyarwanda Română Magyar Čeština Moore Malagasy Oromoo ಕನ್ನಡ Wolof Azərbaycan O‘zbek Українська ქართული Македонски ភាសាខ្មែរ ਪੰਜਾਬੀ मराठी Kirundi Kurmancî Bahasa Melayu Yaoالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለነፍሱ የሚወደውን አምልኮዎችና ሃይማኖታዊም ይሁን ዱንያዊ መልካም ነገሮችን ለወንድሙ እስከሚወድ ድረስ፤ ለነፍሱ የሚጠላውንም ለርሱ እስኪጠላ ድረስ ለአንድ ሙስሊም የተሟላ ኢማን እንደማይረጋገጥ ገለፁ። በሙስሊም ወንድሙ ላይ የዲን ጉድለት ከተመለከተም ለማስተካከል ይታገላል። በርሱ ላይ መልካምን ከተመለከተም ያበረታዋል፣ ያግዘዋል፣ የዲኑን ወይም የዱንያውን ጉዳይም ይመክረዋል።فوائد الحديث
አንድ ሙስሊም ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ የመውደድ ግዴታ እንዳለበት እንረዳለን። ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ የማይወድ ሰው ከርሱ ላይ ኢማን ውድቅ መደረጉ ይህን መተግበር ግዴታ መሆኑን ይጠቁማል።
ለአላህ ብሎ ወንድማማች መሆን ከዘር ወንድማማችነትም በላይ ነው። የኢስላማዊ ወንድማማችነት ግዴታውም የበለጠ ነው።
ይህንን ውዴታ የሚቃረን ሁሉ ማጭበርበር፣ ሀሜት፣ ምቀኝነት፣ በሙስሊም ነፍስ ላይ ወይም ገንዘቡ ላይ ወይም ክብሩ ላይ ጠላት መሆንን የመሳሰሉ ንግግርም ሆነ ተግባርም ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
"ለወንድሙ" ከሚለው ቃል እንደምንረዳው ለአንድ ተግባር የሚያነሳሳ የሆነን ቃል መጠቀም ተገቢ እንደሆነ ነው።
ኪርማኒ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል: «ከዚህም በተጨማሪ ለነፍሱ የሚጠላውን መጥፎ ነገር ለወንድሙ መጥላቱም የኢማን ክፍል ነው። ሐዲሡ ላይ ያልጠቀሱት አንድን ነገር መውደድ ተቃራኒውን መጥላት የሚያስፈርድ ስለሆነ በዚህ በመብቃቃት ነው መጥቀሱን የተዉት።
