አላህ ሁሉም ነገር ላይ መልካምነትን ጽፏል፤

አላህ ሁሉም ነገር ላይ መልካምነትን ጽፏል፤

ከአቡ የዕላ ሸዳድ ቢን አውስ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦ «አላህ ሁሉም ነገር ላይ መልካምነትን ጽፏል፤ ስትገድሉም አሳምራችሁ ግደሉ፤ ስታርዱም አሳምራችሁ እረዱ፤ አንዳችሁ ስለቱን በደንብ ይሞርድና እንሰሳውን ቶሎ ይገላግል።»

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ በኛ ላይ በሁሉም ነገሮች ኢሕሳንን ግዴታ እንዳደረገ ተናገሩ። ማሳመር (ኢሕሳን) ማለት በአምልኮውም ውስጥ፣ መልካምን ሲፈፅምም፣ ከፍጡራን ላይ ጎጂን ነገር ሲያስወግድም ዘውትር አላህ ያየኛል ማለት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በመግደልና በማረድ ውስጥ ማሳመርም አንዱ ነው። በመግደል ኢሕሳን ሲባል በቂሷስ (ሸሪዐዊ የቅጣት ብይን ለምሳሌ የገደለ መገደል) ተፈፃሚነት ወቅት: ለመግደል ገሩን፣ ቀላሉንና የተገዳዩን ነፍስ በፍጥነት ሊያወጣ የሚችለውን መንገድ በመምረጥ ነው። በእርድ ማሳመር ሲባል ደግሞ እንስሳ በምናርድበት ወቅት ነው። ይህም መሳሪያውን በደንብ በመሞረድ ፣ የሚታረደው እንስሳ እያየ ፊት ለፊቱ ባለመሞረድና ሌላ እርዱን የሚመለከት እንስሳ ቦታው ላይ እያለ ባለማረድ ለእንስሳ በማዘን ነው።

فوائد الحديث

የላቀውና የተከበረው አላህ በፍጡራኑ ላይ ያለው እዝነትና ርህራሄን እንረዳለን።

አገዳደልና አስተራረድ ላይ ኢሕሳን የሚባለው ሸሪዐውን የተከተለ (የዋጀ) በሆነ መልኩ ሲፈፀም ነው።

ሸሪዐ ምሉዕና ሁሉንም መልካም ነገር የጠቀለለ ሲሆን ከዚህም መካከል ለእንስሳት ማዘኑና መራራቱ አንዱ ነው።

የሰውን ልጅ ከገደሉ በኋላ ሰውነቱን መቆራረጥ መከልከሉን እንረዳለን።

እንስሳትን ማሰቃየት ያለበት ነገር ሁሉ ክልክል መሆኑን ተረድተናል።