ዓኢሻን እንዲህ በማለት ጠየቅኳት: "የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ፆምን ቀዷ እያወጣች ሶላትን ቀዷ የማታወጣው ለምንድን ነው?

ዓኢሻን እንዲህ በማለት ጠየቅኳት: "የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ፆምን ቀዷ እያወጣች ሶላትን ቀዷ የማታወጣው ለምንድን ነው?

ከሙዓዘህ እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «ዓኢሻን እንዲህ በማለት ጠየቅኳት: "የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ፆምን ቀዷ እያወጣች ሶላትን ቀዷ የማታወጣው ለምንድን ነው?" እርሷም "አንቺ ሐሩሪያ ነሽን?" አለችኝ። እኔም "ሐሩሪያ አይደለሁም። እንዲሁ እየጠየቅኩ ነው።" አልኳት። እርሷም "ይህ ጉዳይ ያጋጥመን ነበር። ፆምን ቀዷ በማውጣት (በማካካስ) ስንታዘዝ ሶላትን ቀዷ በማውጣት ግን አንታዘዝም ነበር።" አለች።»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ሙዓዘተል ዓደዊያህ የአማኞች እናት የሆነችውን ዓኢሻን አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና እንዲህ በማለት ጠየቀቻት: "የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ፆምን ቀዷ እያወጣች ሶላትን ቀዷ የማታወጣው ለምንድን ነው?" እርሷም "አንቺ ለማጥበቅና ለማክበድ ጥያቄን የሚያበዙት ከሆኑት ከኸዋሪጆች ከሐሩሪያዎች ነሽን?" አለቻት። እኔም "ሐሩሪያ አይደለሁም። እንዲሁ እየጠየቅኩ ነው።" አልኳት። እርሷም "ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ሳለን የወር አበባ ያጋጥመን ነበር። ፆምን ቀዷ በማውጣት ስንታዘዝ ሶላትን ቀዷ በማውጣት ግን አንታዘዝም ነበር።" አለች።

فوائد الحديث

ለክርክርና ለማምታታት ጥያቄን የሚጠይቅ ሰው መወገዙን እንረዳለን።

ሐሩሪያ ኩፋ አቅራቢያ ከሚገኝ ቦታ ለሚመጡ ሰዎች የተሰጠ ስያሜ ነው። የከተማዋ ስም "ሐሩራእ" ይባላል። በከተማዋ የሚኖሩትም ከኸዋሪጅ የሆኑ ሰዎች ነበሩ። ዓኢሻ ከነርሱ ጋር ያመሳሰለቻቸውም በጉዳዮች ላይ ስለሚያጠብቁ፣ ጥያቄ ስለሚያበዙ እና ጥያቄያቸውም የድርቅና ስለነበረ ነው።

አስተማሪ የሆነ ሰው ለመማርና ማብራሪያ ፈልጎ እርሱ ጋር የመጣውን አጥርቶ ማስተማር እንደሚገባው እንረዳለን።

የሚጠየቁ ጥያቄዎችን (የቁርኣን ወይም የሐዲሥ) ጥቅስን በመጥቀስ መመለስ በላጭ ስለሆነ ዓኢሻ አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና ጠያቂዋ ለጠየቀችው ጥያቄ የጀርባ ሃሳቡን ለማብራራት አልሞከረችም። ይህንንም ያደረገችው ጥቅስን ብቻ በመጥቀስ መመለስ ተቃውሞን ገቺ ስለሆነ ነው።

ሰውዬው ጥበቡን ባያውቀው እንኳ ለአላህና ለመልክተኛው (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ፍርድ እጅ መስጠት ይገባዋል።

ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "የዓኢሻ አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና አነጋገር መልዕክት ከኸዋሪጆች የተወሰኑ ጭፍሮች የወር አበባ ላይ ያለች ሴት በወር አበባ ወቅት ያመለጣትን ሶላት ቀዷ ማውጣት ግዴታዋ አድርገው እንደሚያምኑ አመላካች ነው። ይህ ግን ከሙስሊሞች ስምምነት ያፈነገጠ አቋም ነው። ዓኢሻ ጠያቂዋን የጠየቀቻት ይህንን በሚተች ስልት ነው። ማለትም ይህ አይነቱ አቋም አስከፊ የሆነው የሐሩሪያዎች አይነት መንገድ ነው።"

التصنيفات

የወር አበባ፣ የወሊድ ደምና የበሽታ ደም, ጾምን ቀዿእ ማውጣት