ከዱንያ ባጠቃላይ በልጣ እኔ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆነች አንቀፅ በኔ ላይ ወረደች።

ከዱንያ ባጠቃላይ በልጣ እኔ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆነች አንቀፅ በኔ ላይ ወረደች።

ከአነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «ሐዘንና ትካዜ ወርሯቸው፣ ቁርባኑንም (ሀድዩን) አርደው ከሑደይቢያ እየተመለሱ ሳሉና {እኛ ላንተ ግልፅ የሆነን መክፈት ከፈትንልህ። አላህ ካንተ ሊምር} ከሚለው {ታላቅ ማግኘት ነው።} እስከሚለው ድረስ [አልፈትሕ: 1 - 5] ያሉት አንቀፆች በወረዱ ጊዜ ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: "ከዱንያ ባጠቃላይ በልጣ እኔ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆነች አንቀፅ በኔ ላይ ወረደች።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

አነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ ሲሉ ተናገሩ: በአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ይህ የአላህ ቃል የወረደ ጊዜ: {(1) እኛ ላንተ ግልፅ የሆነን መክፈት ከፈትንልህ። (2) አላህ ከኀጢአትህ ያለፈውንና የሚመጣውን ላንተ ሊምር ጸጋውንም ባንተ ላይ ሊሞላ ቀጥተኛውንም መንገድ ሊመራህ (ከፈተልህ)። (3) አላህ ብርቱን እርዳታ ሊረዳህም (ከፈተልህ)። (4) እርሱ ያ በምእመናን ልቦች ውስጥ ከእምነታቸው ጋር እምነትን ይጨምሩ ዘንድ እርጋታን ያወረደ ነው። ለአላህም የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አሉት። አላህም አዋቂ ጥበበኛ ነው። (5) ምእመናንንና ምእመናትን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈስባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ ሊያገባቸው ከነርሱም ሀጢአቶቻቸውን ሊያብስላቸው (በትግል አዘዛቸው)። ይህም ከአላህ ዘንድ የሆነ ታላቅ ማግኘት ነው።} [አልፈትሕ: 1-5] እነዚህ አንቀጾች የወረዱትም ሶሓቦች በሑደይቢያ ስምምነቱ መካሄድ ምክንያት ዑምራን ከማድረግ ክልከላ ተጥሎባቸው ሀድያቸውን (ቁርባናቸውን) በሑደይቢያ አርደው ስምምነቱ የሙስሊሞችን ጥቅም ያስጠበቀ አይደለም በሚል ሀዘንና ትካዜ ወርሯቸው ከዛ በሚመለሱበት ወቅት ነበር። ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ አሉ: እኔ ዘንድ ከዱንያ ባጠቃላይ ተወዳጅ የሆነች አንቀፅ በኔ ላይ ወረደች። ቀጥለውም አነበቧት።

فوائد الحديث

አላህ በሑደይቢያ ስምምነት ወቅት ለነቢዩ ሙሐመድ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ትልቅ ድል በመክፈት የዋለላቸው ፀጋ ትልቅ መሆኑ ተገልጿል። ይህንንም በማስመልከት ነው ለርሳቸው እንዲህ ያላቸው: {እኛ ላንተ ግልፅ የሆነን መክፈት ከፈትንልህ።}

ሶሓቦች ረዲየሏሁ ዐንሁም - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ለአላህ ትእዛዝ የተዋደቁና የተገዙ ጊዜ የቸራቸው ነገር ተገልጿል። አላህ እነርሱን በማስመልከትም ይህንን አውርዷል: {ምእመናንንና ምእመናትን ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈስባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ ሊያገባቸው።}

አላህ ለነቢዩና ለአማኞች ድልና መከፈትን ቃል በመግባት የዋለው ችሮታ ተገልጿል።

ሰዕዲይ ይህን አንቀፅ በተፍሲራቸው ውስጥ ሲያብራሩት እንዲህ ብለዋል: "{እኛ ላንተ ግልፅ የሆነን መክፈት ከፈትንልህ።} [አልፈትሕ:1] ይህ የተጠቀሰው መከፈት ማለት የሑደይቢያ ስምምነት ነው። ይህም በረጅሙ ታሪክ እንደተጠቀሰው የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዑምራ ለማድረግ በመጡበት ወቅት አጋርያኖች እርሳቸውን ወደ መካ ላለማስገባት ዘጉባቸው። የጉዳዩ መጨረሻም የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ለአስር አመት ጦርነት የማቆም፤ በቀጣይ አመት ዑምራ ሊያደርጉ፤ ወደ ቁረይሾችና ከነርሱ ጋር የጦር ቃልኪዳን ወደተጋቡት ግዛቶች መግባት የፈለገ ሰው እንዲገባ፤ ወደ አላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ቃልኪዳንና ውል መግባት የፈለገ ሰውም መፈፀም እንደሚችል ከአጋርያን ጋር መስማማት ነበር። በዚህም ምክንያት ሰዎች እርስ በርስ ሲተማመኑ ወደ አላህ ሃይማኖት የሚደረገው ጥሪ ተስፋፋ፤ በነዚህ ግዛቶች በማንኛውም ስፍራ የሚኖር አማኝ የሆነና ለጥሪ የተመቻቸ ከሆነ ስለእስልምና እውነታ ለማወቅ የፈለገን ያሳውቃል። በነዚህ ጊዜያትም ሰዎች በህብረት በህብረት እየሆኑ ወደ አላህ ሃይማኖት ገቡ። ለዚህም ነው አላህ የድል መከፈት ብሎ የሰየመው። ግልፅ የሆነ ድል ብሎም ገለፀው። ይህም የሆነበት የአጋርያንን ሀገራት ድል በማድረግ የሚታለመው የአላህን ሃይማኖት የበላይ ማድረግና የሙስሊሞችን አሸናፊነት ማረጋገጥ ስለሆነ ነው። ይህ ደግሞ በዚህ ስምምነት ብቻ ተገኝቷል።"

التصنيفات

የቁርአን ማብራሪያ, የቁርአን ትሩፋቶች