ሶላትን አደራ! በእጆቻችሁ ስር ያሉትን (ባሪያዎችን) አደራ!

ሶላትን አደራ! በእጆቻችሁ ስር ያሉትን (ባሪያዎችን) አደራ!

ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጣዕረ ሞት ባጋጠማቸው ጊዜ አብዝተው ይመክሩት የነበሩት ምክር " ሶላትን አደራ! በእጆቻችሁ ስር ያሉትን (ባሪያዎችን) አደራ! ሶላትን አደራ! በእጆቻችሁ ስር ያሉትን (ባሪያዎችን) አደራ!" የሚል ነበር። የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ይህን ምክር ከልባቸው ጉሮሯቸው ድረስ እስኪተናነቃቸው ደጋግመው ይሉት ነበር። ነገር ግን ምላሳቸው ልታወጣው ይሳናቸው ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።]

الشرح

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጣዕረ ሞት ላይ ሳሉ ለኡመታቸው አብዝተው ይመክሩት የነበረው ምክር: "ሶላትን አጥብቃችሁ ያዙ፤ በመስገዱም ላይ ተጠባበቁ፤ ከሶላትም አትዘናጉ። ልክ እንደዚሁ በእጆቻችሁ ስር ያሉትን ባሪያዎችንም መብት ጠብቁ። ለባሮቻችሁ በጎ ስሩ።" የሚል ነበር። ይህንን ምክር ሲሉም ጉሮሯቸውን እስኪተናነቃቸው ድረስ ከመደጋገም አልተወገዱም። ምላሳቸውም ቃሉን ለማውጣት ይሳነው ነበር።

فوائد الحديث

የሶላትና የባሪያዎች መብት ጉዳይ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከመከሯቸው ምክሮች የመጨረሻዎቹ ምክር መሆናቸው የሶላትና የባሪያዎች መብት ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ ያስረዳናል።

ሶላት አላህ በባሮቹ ላይ ካሉት ሐቆች መካከል ትልቁ ሐቅ ነው። የፍጡራንን ሐቅ መወጣት በተለይ የደካሞችና ከልጆቻችን ውጪም ቢሆኑ በእጆቻችን ስር የምናስተዳድራቸውን ሰዎች ሐቅ መጠበቅ ከትላልቅ የፍጡራን ሐቆች መካከል አንዱ ነው።

التصنيفات

የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ህልፈት, የሶላት ግዴታነትና የተወው ሰው ፍርድ