إعدادات العرض
ሐላል (የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው።
ሐላል (የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው።
ከአቡ ዐብደላህ ኑዕማን ቢን በሺር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: "ሐላል (የተፈቀደ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። ሐራሙም (እርም የተደረገ) ነገር ሁሉ ግልፅ ነው። በመካከላቸው አብዛኛው ሰዎች የማያውቃቸው አሻሚ ጉዳዮች አሉ። አሻሚ ጉዳዮችን የተጠነቀቀ ሰው ሃይማኖቱንና ክብሩን ጠብቋል። አሻሚ ጉዳዮች ላይ የወደቀም ሰው ሐራም ላይ ወድቋል። የዚህ ሰው አምሳያ ልክ የተከለከለ ክልል ወሰን ዙሪያ እንደሚጠብቅና እንስሳዎቹም ወሰን አልፈው የተከለከለው ክልል ውስጥ ሊገቡ እንደቀረቡበት እረኛ ነው። አዋጅ! ለሁሉም ንጉስ ወሰን (ድንበር) አለው። አዋጅ! የአላህ ወሰን (ድንበር) ደግሞ ክልከላው ነው። አዋጅ! ሰውነት ውስጥ የምትገኝ ቁራጭ ስጋ አለች። እሷ ከተስተካከለች ሁሉም ሰውነት ይስተካከላል። እሷ ከተበላሸች ደግሞ ሁሉም ሰውነት ይበላሻል። አዋጅ! እሷም ልብ ናት።"
[ሶሒሕ ነው።] [رواه البخاري ومسلم]
الترجمة
العربية Español English اردو Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Français Türkçe Русский Bosanski සිංහල हिन्दी 中文 فارسی Tiếng Việt Tagalog Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ ไทย Deutsch 日本語 پښتو অসমীয়া Shqip Svenska Nederlands ગુજરાતી Кыргызча नेपाली Yorùbá Lietuvių دری Српски Soomaali тоҷикӣ Kinyarwanda Română Magyar Čeština Moore Malagasy Fulfulde Italiano Oromoo ಕನ್ನಡ Wolof Български Azərbaycan Ελληνικά Akan O‘zbek Українська ქართული Lingala Македонски ភាសាខ្មែរ Bambara ਪੰਜਾਬੀ मराठी Kirundi Kurmancî Bahasa Melayu Yaoالشرح
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለነገሮች ሁሉ የሚያገለግል አጠቃላይ መርህን እያብራሩ ነው። ነገሮች ሁሉ በሸሪዐ መሰረት ወደ ሶስት ክፍሎች ይከፈላሉ: ግልፅ ሐላል ፣ ግልፅ ሐራምና ከፍቁድነትና ክልክልነት አንፃር ብዙ ሰው ብይናቸውን የማያውቃቸው ግልፅ ያልሆኑ አሻሚ ጉዳዮች ናቸው። በሱ ላይ አሻሚ የሆኑበትን ጉዳዮች የተወ ሰው ሀራም ላይ ከመውደቅ በመራቁ ሳቢያ እምነቱ ሰላም ይሆናል፤ ይህን አሻሚ የሆነ ጉዳይ በመፈፀሙ ሳቢያ እሱ ላይ የሚደርስን የሰዎች ትችት ስለማይኖርም ክብሩ ከትችት ሰላም ይሆናል። አሻሚ ጉዳዮችን ያልራቀ ሰው ግን ወይ ሐራም ላይ በመውደቅ ወይ በሰዎች ክብሩ በመዘለፉ ሳቢያ ነፍሱን (ለችግር) ያጋልጣታል። መልክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አሻሚ ጉዳዮች የሚፈፅምን ሰው ሁኔታ ለማብራራት ምሳሌ ጠቀሱ። እሱም ልክ ባለቤቱ በከለላት ስፍራ አስጠግቶ ከብቶቹን እንደሚያሰማራ እረኛ ነው። ቀስ በቀስ የእረኛው ከብቶች ወደተከለለው ስፍራ ቅርብ ስለሆኑ ክልሉ ውስጥ ዘልቀው ሊበሉ ይቀርባሉ። ልክ እንደዚሁ አሻሚ የሆኑ ጉዳዮችን የሚሰራ ሰው በዚህ መዳፈሩ ሳቢያ ወደ ሐራም ይቃረባል። ቀስበቀስ ሐራም ውስጥ ሊወድቅም ይቀርባል። ቀጥለውም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሰውነት ውስጥ የምትገኝ ቁራጭ ስጋ እንዳለች ገለፁ። (እሷም ልብ ናት።) በሷ መስተካከል ሰውነት ይስተካከላል በሷ መበላሸትም ሰውነት ይበላሻል።فوائد الحديث
ይህ ሐዲሥ ተመሳሳይ (የሚያምታቱ) የሆኑ ነገሮችን ለመጠንቀቅ መርህ የሆነ ሐዲሥ ነው።
ብይናቸው ግልፅ ያልሆኑ አሻሚ ጉዳዮችን መተው መበረታታቱን እንረዳለን።
