በሰጋጅ ፊት የሚያልፍ ሰው በርሱ ላይ ያለበትን ወንጀል ቢያውቅ ኖሮ በሰጋጅ ፊት ከማለፍ ይልቅ አርባ መቆም ለርሱ መልካም ይሆንለት ነበር።

በሰጋጅ ፊት የሚያልፍ ሰው በርሱ ላይ ያለበትን ወንጀል ቢያውቅ ኖሮ በሰጋጅ ፊት ከማለፍ ይልቅ አርባ መቆም ለርሱ መልካም ይሆንለት ነበር።

ከቡስር ቢን ሰዒድ እንደተላለፈው: ዘይድ ቢን ኻሊድ አልጁሃኒይ -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- ቡስር ቢን ሰዒድን ወደ አቡ ጁሃይም -አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና- በሰጋጅ ፊት ስለማለፍ ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ምን እንደሰማ ሊጠይቀው ላከው። አቡ ጁሃይምም እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል: "በሰጋጅ ፊት የሚያልፍ ሰው በርሱ ላይ ያለበትን ወንጀል ቢያውቅ ኖሮ በሰጋጅ ፊት ከማለፍ ይልቅ አርባ መቆም ለርሱ መልካም ይሆንለት ነበር።" አቡ ነድር እንዲህ ብሏል" አርባ ሲል አርባ ቀን ወይም ወር ወይም ዓመት እንደሆነ አላውቅም።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ግዴታም ይሁን ሱና ሶላት በሚሰግድ ሰው ፊት ከማለፍ አስጠነቀቁ። ሆን ብሎ ይህንን የሚፈፅም ሰው የሚኖርበትን ወንጀል ቢያውቅ ኖሮ አርባ መቆምን ይመርጥ ነበር። በሰጋጅ ፊት ከሚያልፍ ይልቅ ይህ ይሻለው ነበር። ይህንን ሐዲሥ ያወራው አቡ ነድር እንዲህ አለ: አርባ ቀን ነው ወይስ ወር ወይስ አመት የሚለውን አላውቅም።

فوائد الحديث

ሰጋጁ ሱትራ (መከለያ) ከሌለው በሰጋጅ ፊት ማለፍ ክልክል ነው። ወይም ሱትራ (መከለያ) ካለው ደሞ በርሱና በመከለያው መካከል ማለፍ ክልክል ነው።

ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ርቀቱን በመወሰን ዙሪያ ልዩነቶች ተስተናግደዋል። በርሱና ሱጁድ በሚያደርግበት ቦታ መካከል ባለው ርቀት ውስጥ ነው ተብሏል፤ በርሱና በሶስት ክንድ መካከል ማለፍ ነውም ተብሏል፤ በርሱና ድንጋይ ተወርውሮ በሚያርፍበት መካከል ባለው ርቀት ውስጥ ማለፍ ነውም ተብሏል።"

ሱዩጢይ እንዲህ ብለዋል: "ማለፍ በማለት የተፈለገው ከፊት ለፊቱ በአግድመት ማለፉ ነው። ከፊት ለፊቱ ወደ ቂብላ አቅጣጫ ቢሄድ ግን ሐዲሡ ውስጥ ያለው ዛቻ አይመለከተውም።"

ለሰጋጁ ሶላቱን ለጉድለት እንዳያጋልጥና አላፊውንም ለወንጀል እንዳይዳርገው በላጩ ሰዎች በሚተላለፉበት መንገድና ሰዎች የግዳቸውን በሚያልፉበት ስፍራ አለመስገዱ ነው። እንዲሁም በርሱና በሚያልፉ ሰዎች መካከል መከለያና ግርዶሽ አድርጎ መስገድ ነው።

ከዚህ ሐዲሥ ከምንወስዳቸው ፋይዳዎች መካከል በመጪው አለም ወንጀልን ተከትሎ የሚያጋጥመን ቀላሉ የሀጢአት ቅጣት በዱንያ ከሚያጋጥሙ ከባባድ ችግሮችም የከበደ መሆኑን ነው።

التصنيفات

የሶላት ሱናዎች