ሰዎች ሶላታቸው ውስጥ ሆነው ዓይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርጉት ምን ሆነው ነው!?" በዚህ ዙሪያም አጠንክረው አስጠነቀቁ። እንዲህም አሉ "ከዚህ ተግባራቸው ይከልከሉ ወይም አይናቸው…

ሰዎች ሶላታቸው ውስጥ ሆነው ዓይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርጉት ምን ሆነው ነው!?" በዚህ ዙሪያም አጠንክረው አስጠነቀቁ። እንዲህም አሉ "ከዚህ ተግባራቸው ይከልከሉ ወይም አይናቸው ትነጠቃለች።

ከአነስ ቢን ማሊክ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "ሰዎች ሶላታቸው ውስጥ ሆነው ዓይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርጉት ምን ሆነው ነው!?" በዚህ ዙሪያም አጠንክረው አስጠነቀቁ። እንዲህም አሉ "ከዚህ ተግባራቸው ይከልከሉ ወይም አይናቸው ትነጠቃለች።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሶላት ውስጥ ሆነው ዱዓ ሲያደርጉም ይሁን ሌላ ድርጊት ሲያደርጉ አይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርጉ ሰዎችን አስጠነቀቁ። ቀጥለውም ይህንን በሚፈፅሙ ሰዎች ላይ ማስጠንቀቂያቸውንና ዛቻቸውን አበረቱ። በማያውቁት መልኩ የማየትን ፀጋ በሚያጡበት ሁኔታ አይኖቻቸውን የመነጠቅና በፍጥነት የመጥፋት አደጋ እንደሚፈራለትም አሳሰቡ።

فوائد الحديث

የነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጥሪ ያማረ መሆኑንና እውነትን ባመረ መልኩ እንደሚያብራሩ ተረድተናል። የነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አላማ እውነቱን መግለፅ ስለሆነና ያንንም ስላሳኩ ይህንን የተቃረነውን ግለሰብ አላጋለጡትም። ይህን በማድረጋቸውም የተቃረነውን ግለሰብ ነውሩ ተሸሽጎለት እንዲቀበልም ይጋብዘዋል።

ሶላት ውስጥ አይኑን ወደ ሰማይ ከፍ ባደረገ ሰው ላይ ጠንካራ ክልከላና ከባድ ዛቻ መምጣቱን እንረዳለን።

ዐውነል መዕቡድ ውስጥ እንዲህ ተብራርቷል: "የዚህ ምክንያትም ዓይኑን ወደ ሰማይ ከፍ ያደረገ ጊዜ ከቂብላ መስመር መውጣት፤ ሶላቱና አፈፃፀሙንም ችላ ማለት ስለሆነ ነው።"

ሰላት ውስጥ ዓይንን ወደላይ ማንጋጠጥ ከተመስጦ ጋር ይቃረናል።

የሶላት ጉዳይ የላቀ እንደሆነ እንረዳለን። ሰጋጅ የሆነ ሰውም ሶላት ውስጥ ከአላህ ጋር በተሟላ ስርዓት መቅረብ ግዴታው እንደሆነ እንረዳለን።

التصنيفات

የሰጋጆች ስህተት