إعدادات العرض
ከጀሀነም ነዋሪዎች መካከል እጅግ ዝቅተኛ ቅጣት የሚቀጣው ለርሱ ሁለት የእሳት ጫማዎችና የጫማ ማሰሪያዎች የሚደረግለት ነው። በነርሱም ምክንያት ድስጥ እንደሚንፈቀፈቀው አንጎሉ…
ከጀሀነም ነዋሪዎች መካከል እጅግ ዝቅተኛ ቅጣት የሚቀጣው ለርሱ ሁለት የእሳት ጫማዎችና የጫማ ማሰሪያዎች የሚደረግለት ነው። በነርሱም ምክንያት ድስጥ እንደሚንፈቀፈቀው አንጎሉ ይንፈቀፈቃል። ከርሱ የበለጠ ቅጣት የሚቀጣ አንድም ሰው አለ ብሎም አያስብም። እርሱ እየተቀጣ ያለው ግን እጅግ ዝቅተኛውን ቅጣት ነው።
ከኑዕማን ቢን በሺር (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦ "ከጀሀነም ነዋሪዎች መካከል እጅግ ዝቅተኛ ቅጣት የሚቀጣው ለርሱ ሁለት የእሳት ጫማዎችና የጫማ ማሰሪያዎች የሚደረግለት ነው። በነርሱም ምክንያት ድስጥ እንደሚንፈቀፈቀው አንጎሉ ይንፈቀፈቃል። ከርሱ የበለጠ ቅጣት የሚቀጣ አንድም ሰው አለ ብሎም አያስብም። እርሱ እየተቀጣ ያለው ግን እጅግ ዝቅተኛውን ቅጣት ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Kurdî Kiswahili Português සිංහල Nederlands Tiếng Việt অসমীয়া ગુજરાતી پښتو Hausa ไทย മലയാളം नेपालीالشرح
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የትንሳኤ ቀን እጅግ ዝቅተኛ ቅጣት የሚቀጣው የእሳት ነዋሪ ለርሱ ሁለት የእሳት ጫማዎችና ማሰሪያዎች የሚደረግለት ሰው እንደሆነና ከአቃጣይነታቸው የተነሳ የነሃስ ድስጥ እንደሚንፈቀፈቀው አንጎሉም የሚንፈቀፈቅ መሆኑን፤ ከርሱ የበለጠ የሚቀጣ አንድም ሰው አለ ብሎም እንደማያስብ፤ እርሱ ግን እጅግ ዝቅተኛውን ቅጣት የሚቀጣ ነው መሆኑን ተናገሩ። ይህንን የሚያስበውም አካላዊ ቅጣቱ ከመንፈሳዊ ቅጣቱ ጋር በጋራ እንዲቀጣበት ነው።فوائد الحديث
ከሃዲያንና ወንጀለኞች ከዚህ የእሳት ውስጥ የቅጣት ጭንቀት መጠንቀቅ እንዳለባቸው እንረዳለን። ይህም ይህን ከሚያስከትልባቸው ነገር እንዲርቁ ነው።
እሳት የሚገቡ ሰዎች ደረጃ እንደየ መጥፎ ስራቸው መጠን እንደሚለያይ እንረዳለን።
አላህ ከርሷ ነፃ ያውጣንና የእሳት ቅጣት ከባድነትን እንረዳለን።
التصنيفات
የጀነትና እሳት ባህሪዎች