إعدادات العرض
ቀድሞ ቀመስን በመቀነስ፣ ጥፍርን በመቁረጥ፣ የብብት ፀጉርን በመንጨትና ብልት አካባቢ የሚበቅልን ፀጉር በመላጨት ዙሪያ ከአርባ ቀናት በላይ ሳናስወግድ እንዳንተወው የጊዜ ገደብ…
ቀድሞ ቀመስን በመቀነስ፣ ጥፍርን በመቁረጥ፣ የብብት ፀጉርን በመንጨትና ብልት አካባቢ የሚበቅልን ፀጉር በመላጨት ዙሪያ ከአርባ ቀናት በላይ ሳናስወግድ እንዳንተወው የጊዜ ገደብ ተቀመጠልን።
አነስ ቢን ማሊክ ረዲየሏሁ ዐንሁ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንዲህ አሉ፦ "ቀድሞ ቀመስን በመቀነስ፣ ጥፍርን በመቁረጥ፣ የብብት ፀጉርን በመንጨትና ብልት አካባቢ የሚበቅልን ፀጉር በመላጨት ዙሪያ ከአርባ ቀናት በላይ ሳናስወግድ እንዳንተወው የጊዜ ገደብ ተቀመጠልን።"
الترجمة
العربية Tiếng Việt Bahasa Indonesia Nederlands Kiswahili English অসমীয়া ગુજરાતી සිංහල Magyar ქართული Hausa Română ไทย Português తెలుగు मराठी ភាសាខ្មែរ دری বাংলা Kurdîالشرح
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ወንድ ልጅ ቀድሞ ቀመሱን ለመቀነስ፣ የእጆችና እግሮችን ጥፍሮች ለማሳጠር፣ የብብትን ፀጉር ለመንጨትና ብልት አካባቢ የሚበቅለውን ፀጉር ለመላጨት ከአርባ ቀናት በላይ ሳይቆረጥ እንዳይተው የጊዜ ገደብ አስቀመጡ።فوائد الحديث
ሸውካኒይ እንዲህ ብለዋል: "ተመራጩ አቋም የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በመጠኑት አርባ ቀን ይገደባል የሚለው ነው። ከዚህ በላይ ማሳለፍም አይፈቀድም። እየረዘመ እንኳ ይህ የጊዜ ገደብ እስኪጠናቀቅ ማሳጠርና መላጨት የተወ ሰው ሱናን ተፃራሪ ተደርጎ አይቆጠርም።"
ኢብኑ ሁበይራ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ይህንን የማዘግየት የመጨረሻው ቀነ ገደቡ ነው። የተሻለው ግን ይህንን የመጨረሻ ቀነ ገደብ ሳይደርስ በፊት መቁረጥ ነው።"
እስልምና ንፅህና፣ መፅዳትና ውበት ላይ ትኩረት ማድረጉን እንረዳለን።
ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር የሚፈፀመው የላይኛው ከንፈር ላይ የሚበቅልን የተወሰነን ፀጉር በመቁረጥ ነው።
የብብትን ፀጉር መንጨት የሚፈፀመው ብብት ላይ የሚበቅልን ፀጉር በማስወገድ ነው። ብብት የሚባለውም በጡንቻና በትከሻ መካከል የሚለየው አጥንት ስር የሚገኝ ስፍራ ነው።
የብልት ፀጉርን መላጨት ማለት በወንድም ይሁን በሴቶች ብልት ዙሪያ የሚበቅልን ሸካራ ፀጉር መላጨት ማለት ነው።
التصنيفات
ተፈጥሯዊ ሱናዎች