إعدادات العرض
እስልምና በአምስት መሰረቶች ተገነባ
እስልምና በአምስት መሰረቶች ተገነባ
ከአቡ ዐብዱረሕማን ዓብደላህ ቢን ዑመር ቢን ኸጧብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ: «እስልምና በአምስት መሰረቶች ተገነባ እነርሱም: 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወአንነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ' (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ሙሐመድም የአላህ ባሪያና መልክተኛ ናቸው።) ብሎ መመስከር፣ ሶላትን ማቋቋም፣ ዘካ መስጠት፣ በተከበረው የአሏህ ቤት ሐጅ ማድረግ እና የረመዷንን ወር መፆም ናቸው።»
[ሶሒሕ ነው።] [رواه البخاري ومسلم]
الترجمة
العربية Español English اردو Indonesia ئۇيغۇرچە বাংলা Français Türkçe Русский Bosanski සිංහල हिन्दी 中文 فارسی Tiếng Việt Tagalog Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ ไทย Deutsch 日本語 پښتو অসমীয়া Shqip Svenska Nederlands ગુજરાતી Кыргызча नेपाली Yorùbá Lietuvių دری Српски Soomaali тоҷикӣ Kinyarwanda Română Magyar Čeština Moore Malagasy Fulfulde Oromoo ಕನ್ನಡ Wolof Azərbaycan O‘zbek Українська ქართული Македонски ភាសាខ្មែរ Bambara ਪੰਜਾਬੀ मराठी Kirundi Kurmancî Bahasa Melayu Yaoالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ኢስላምን አምስት አስተማማኝ ምሶሶዎች እንደተሸከሙት ቤት አድርገው መሰሉት። የተቀሩት የኢስላም ጉዳዮች ደግሞ ቤቱን እንደሚያሟሉ ነገሮች ናቸው። ከእነዚህ ማእዘናት የመጀመሪያው: ሁለቱ የምስክርነት ቃላት ናቸው። እነርሱም: ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን መመስከር ነው። እነዚህ ሁለቱ የምስክርነት ቃላት እንደ አንድ ማእዘን ናቸው። አንዱ ከሌላኛው ተለይቶ የሚታይ አይደለምና። የአላህን ብቸኛ መሆንና ከርሱ ውጪ ያለውን ትቶ በብቸኝነት ለአምልኮ የተገባው እርሱ ብቻ መሆኑን በማመን፣ የሚያስፈርዱትን በመተግበር፣ በሙሐመድ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መልዕክተኝነታቸውን በማመንና እርሳቸውን በመከተል አንድ ባሪያ እነዚህን ሁለት የምስክርነት ቃላት ይናገራል። ሁለተኛው ማእዘን: በቀንና በምሽት የሚሰገዱ የሆኑት የፈጅር፣ የዙህር፣ የዐስር፣ የመጝሪብ እና የዒሻእ ሶላቶችን መስፈርቶቹን፣ ማእዘናቶቹንና ግዴታዎቹን ጠብቆ ማቋቋም ነው። ሶስተኛው ማእዘን: ግዴታ የሆነውን ዘካ ማውጣት ነው። ይህም ገንዘቡ በሸሪዓ የተወሰነውን ያህል መጠን የደረሰ ባለገንዘብ በሙሉ ለሚገባው አካል ሊሰጥ ግዴታ የተደረገበት ገንዘባዊ አምልኮ ነው። አራተኛው ማእዘን: ሐጅ ነው። እርሱም: አምልኳዊ በሆነ መልኩ የሐጅ ተግባራትን ለመፈፀም መካን ማሰብ ነው። አምስተኛው ማእዘን: ረመዷንን መፆም ነው። እርሱም: አላህን በማምለክ ኒያ ጎህ ከወጣችበት ሰአት ጀምሮ ፀሀይ እስከምትጠልቅ ድረስ ከመብላት፣ ከመጠጣትና ሌሎችም ፆምን ከሚያስፈጥሩ ነገሮች መቆጠብ ማለት ነው።فوائد الحديث
ሁለቱ የምስክርነት ቃላቶች አንደኛው በሌላኛው ካልሆነ በቀር አትበቃምና ተያያዥ መሆናቸውን እንረዳለን። ሸሪዓ እንደ አንድ ማእዘን ያደረጋቸውም ለዛ ነው።
የሃይማኖቱ መሰረቶች ሁለቱ የምስክርነት ቃላት ናቸው። ስለሆነም አንዲትም ንግግር ሆነች ተግባር ያለነርሱ ተቀባይነት የላትም።
