إعدادات العرض
የምትችሉትን ስራ ያዙ። በአላህ እምላለሁ። (መስራት) እስክትሰለቹ ድረስ አላህ (ምንዳ ከመስጠት) አይሰለችም።" አሉ።
የምትችሉትን ስራ ያዙ። በአላህ እምላለሁ። (መስራት) እስክትሰለቹ ድረስ አላህ (ምንዳ ከመስጠት) አይሰለችም።" አሉ።
የአማኞች እናትና የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለቤት ከሆነችው ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው: «የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከዓኢሻ ጋር ሆነው ሳሉ ሐውላእ ቢንት ቱወይት ቢን ሐቢብ ቢን አሰድ ቢን ዐብዲልዑዛ በዓኢሻ በኩል አለፈች። እኔም "ይህቺ ሐውላእ ቢንት ቱወይት ናት። እርሷም ሌሊት እንደማትተኛ ገለፁልኝ።" አልኳቸው። የአላህ መልክተኛም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "ሌሊት አትተኛም?! የምትችሉትን ስራ ያዙ። በአላህ እምላለሁ። (መስራት) እስክትሰለቹ ድረስ አላህ (ምንዳ ከመስጠት) አይሰለችም።" አሉ።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tagalog ئۇيغۇرچە Hausa Kurdî Tiếng Việt Magyar ქართული සිංහල Kiswahili Română অসমীয়া ไทย Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
የአማኞች እናት ዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ዘንድ ሐውላእ ቢንት ቱወይት - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነበረች። ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ሲገቡ እርሷ ወጣች። ዓኢሻም እንዲህ አለቻቸው: ይህቺ ሴት ሌሊት አትተኛም። ይልቁንም ሌሊቱን በሙሉ የምታሳልፈው በሶላት ነው። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በራሷ ላይ ማክበዷን በማውገዝ እንዲህ አሉ: ሌሊት አትተኛም?! ከመልካም ስራ መዘውተር የምትችሉትን ያህል ብቻ በመስራት ተጠመዱ። በአላህ እምላለሁ! አላህ ባሮቹ ስራን ከመስራት እስኪሰለቹ እና እስኪተዉ ድረስ ለደጋግና ታዛዥ ባሮቹ በአምልኳቸው፣ በመልካምና በጎ ስራዎቻቸው ምንዳና አጅር ከመስጠት አይሰለችም።فوائد الحديث
ሰውነት ከሚችለው በላይ አምልኮን ማብዛት ሰውነትን ወደ ስልቹነትና ድካም በማምራት ነፍስ አምልኮውን እንድትተወው ያደርጋታል።
አምልኮን ሚዛናዊ አድርጎ መፈፀም በአምልኮው ላይ ቀጣይነትና ፅናት እንዲኖር ያደርጋል።
ዘውታሪ የሆነ ትንሽ ስራ ብዙ ከሆነ የሚቆራረጥ ስራ የተሻለ ነው።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ከባድ የሆነን ብዙ ስራን ከመስራት በተቃራኒ አላህን በማውሳት፣ በመጠባበቅ፣ በኢኽላስና ወደ አላህ ራስን በማዞር ጥቂት ስራ ላይ መዘውተር አምልኮው ዘለቄታ እንዲኖረው ያደርጋል። ዘውትር የተሰራው ጥቂቱ ስራ ተቆራርጦ ከተሰራው ብዙ ስራ በብዙ እጥፍ እስኪበልጥ ድረስ ይነባበራልና።"
التصنيفات
የሰው መብቶች በኢስላም