إعدادات العرض
የሙስሊምን ሰው ገንዘብ ለመውሰድ እየዋሸ የማለ ሰው አላህ በርሱ ላይ የተቆጣበት ሆኖ ይገናኛል።
የሙስሊምን ሰው ገንዘብ ለመውሰድ እየዋሸ የማለ ሰው አላህ በርሱ ላይ የተቆጣበት ሆኖ ይገናኛል።
ከዐብደላህ ቢን መስዑድ ረዲየሏሁ ዓንሁ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድለላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "የሙስሊምን ሰው ገንዘብ ለመውሰድ እየዋሸ የማለ ሰው አላህ በርሱ ላይ የተቆጣበት ሆኖ ይገናኛል።" አሽዓሥም እንዲህ አለ: "በአላህ እምላለሁ! ይህንን የተናገሩት በኔ ምክንያት ነበር። በኔና በአንድ አይሁድ መካከል የመሬት ውል ነበረንና ካደኝ። ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ዘንድም ለፍርድ አቆምኩት። የአላህ መልክተኛም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- "ማስረጃ አለህን?" አሉኝ። እኔም "የለኝም።" አልኩኝ። ከዛም ለአይሁዱ "ማል።" አሉት። እኔም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንዲህ ከሆነማ ምሎ ገንዘቤን ይወስዳል።" አልኳቸው። አላህም {እነዚያ በአላህ ቃል ኪዳንና በመሐላዎቻቸው ጥቂትን ዋጋ የሚለውጡ ... } ሙሉ አንቀፁን አወረደ።"»
الترجمة
العربية Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Türkçe اردو 中文 हिन्दी Português മലയാളം Kurdî Tiếng Việt Nederlands Kiswahili অসমীয়া ગુજરાતી සිංහල Magyar ქართული Hausa Română ไทย मराठी ភាសាខ្មែរ دری বাংলা Македонскиالشرح
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የሚምለው ሰው ውሸቱን እንደሆነ እያወቀ በመሃላው የሌላን ሰው ገንዘብ ለመውሰድ በአላህ መማልን አስጠነቀቁ። ይህ ሰውም አላህ የተቆጣበት ሆኖ ይገናኛል። አሽዓሥ ቢን ቀይስም ረዲየሏሁ ዐንሁ የዚህን ንግግር ሰበብ ሲገልፅ እንዲህ አለ: ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ይህንን የተናገሩት በኔና በአንድ አይሁድ ሰውዬ መካከል በመሬት ባለቤትነት ጉዳይ ጭቅጭቅ ስለነበረን ነው። ወደ ነቢዩም ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ለመፋረድ ሄድን። ለአሽዓሥም እንዲህ አሉት: "የከሰስከው ነገር ላንተ እንዲፈረድ ማስረጃ ማምጣት አለብህ። ይህንን ካልቻልክ የከሰስከው ተከሳሽህ መሃላው ካልያዘው በቀር ላንተ ምንም መብት የለህም።" አሽዓሥም እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እንዲህ ከሆነማ ይህ አይሁድ ሰውዬ ምንም ሳይገደው ምሎ ገንዘቤን ይወስዳል።" አላህም ይህንን ንግግር በቁርአን ለማረጋገጥ ይህንን አወረደ: {እነዚያ በአላህ ቃል ኪዳን የሚለውጡ} ትእዛዙ አማኞች አደራን እንዲወጡ እያዘዘ ነው። {በመሃሎቻቸውም (የሚለውጡ)} በውሸት በስሙ የሚምሉ {ጥቂትን ዋጋ} የዱንያን ስብርባሪ ለማግኘት {እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም ምንም ዕድል የላቸውም።} ምንም ዕጣ የላቸውም። {በትንሳኤ ቀንም አላህ አያነጋግራቸውም።} የሚያስደስታቸውንና የሚጠቅማቸውን ንግግር አያናግራቸውም። ይልቁንም ይቆጣባቸዋል። {የትንሳኤ ቀን ወደነርሱ አይመለከትም።} የእዝነትና የበጎነት እይታን አይመለከታቸውም። {አያነፃቸውምም።} በመልካም እያወሳ አያነፃቸውም። ከወንጀልና ከርክሰትም በምህረቱ አያጠራቸውም። {ለነርሱም አሳማሚ ቅጣት አላቸው።} በፈፀሙት ወንጀል ምክንያት አሳማሚ ቅጣት አላቸው።فوائد الحديث
የሰዎችን ገንዘብ በውሸት መጠቀም ክልክል መሆኑን እንረዳለን።
የሙስሊም ሐቅ አነሰም በዛም ከባድ መሆኑን እንረዳለን።
ማስረጃ ማምጣት የሚጠበቅበት ከሳሽ ሲሆን መሀላ የሚጠበቅበት ደግሞ ክሱን ያስተባበለው ተከሳሽ ነው።
እውነት የሚረጋገጠው በምስክሮች ነው። ከሳሽ ማስረጃ ካላገኘ ግን ተከሳሽ መማል ይጠበቅበታል።
የውሸት መሃላ (የሚን አልጘሙስ) ክልክል መሆኑን እንረዳለን። (የሚን አልጘሙስ) ማለት ማዩ የሌላን ሰው ሐቅ ለመውሰድ በውሸት የሚምለው መሃላ ነው። ይህም ሰውዬውን ለአላህ ቁጣና ቅጣት የሚያጋልጥ ከትላልቅ ወንጀል የሚመደብ ነው።
ዳኛ ለተካሳሾች መምከር እንደሚገባው እንረዳለን። በተለይ ደግሞ ከተከሳሾች መሃላ በሚያስፈልግበት ወቅት መምከር ይገባዋል።