አንድ ሰውዬ ነበር። ከርሱ የበለጠ ቤቱ ከመስጂድ የራቀ አንድም ሰው አላውቅም። ሆኖም አንድም ሶላት አታመልጠውም ነበር።

አንድ ሰውዬ ነበር። ከርሱ የበለጠ ቤቱ ከመስጂድ የራቀ አንድም ሰው አላውቅም። ሆኖም አንድም ሶላት አታመልጠውም ነበር።

ከኡበይ ቢን ከዕብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «አንድ ሰውዬ ነበር። ከርሱ የበለጠ ቤቱ ከመስጂድ የራቀ አንድም ሰው አላውቅም። ሆኖም አንድም ሶላት አታመልጠውም ነበር። ለርሱም እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀረበለት ‐ ወይም እንዲህ ብየ ጠየቅኩት ‐ : "እንደው በጨለማና ቀን ላይ መሬቱ በሚግልበት ወቅት የምትጋልበው አህያ ብትገዛ አይሻልም?" እርሱም "ቤቴ ከመስጂዱ ጎን ቢሆን አያስደስተኝም። እኔ ወደ መስጂድ ስመጣ የምራመደው እርምጃና ወደ ቤተሰቦቼ ስመለስም የምራመደው እርምጃ እንዲፃፍልኝ እፈልጋለሁ።" አለ። የአላህም መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "በርግጥም አላህ ይህንን ሁሉ ላንተ ሰብስቦልሃል።" አሉት።»

[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ኡበይ ቢን ከዕብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተናገሩት: "አንድ ቤቱ ከመስጂደ ነበዊይ እጅግ የራቀ ከአንሷር የሆነ ሰውዬ ነበር። አንድም ሶላት አታመልጠውም ነበር። ይልቁኑም ሁሉንም ሶላት ከነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ተገኝቶ ይሰግድ ነበር። ለርሱም እንዲህ ተባለ: እንደው በምሽቱ ጨለማና ቀን ላይ መሬቱ በሚግልበት ወቅት የምትጋልበው አህያ ብትገዛ አይሻልም? እርሱም እንዲህ አለ: "ቤቴ ከመስጂዱ ጎን ቢሆን አያስደስተኝም። እኔ ወደ መስጂድ ስመጣ የምራመደው እርምጃና ወደ ቤተሰቦቼ ስመለስም የምራመደው እርምጃ እንዲፃፍልኝ እፈልጋለሁ።" አለ። ንግግሩም ነቢዩ ዘንድ ደረሰ። እርሳቸውም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: "በርግጥም አላህ ይህንን ሁሉ ላንተ ሰብስቦልሃል።"

فوائد الحديث

ሶሓቦች ለመልካም ነገር፣ መልካምን ለመጨመርና ምንዳን ለመሸመት የነበራቸው ጥረት ከፍተኛ እንደነበር እንረዳለን።

ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ወደ መስጂድ ሲሄድ በእርምጃው ምንዳ እንደሚያገኘው ሁሉ ከመስጂድ ሲመለስም ምንዳ እንደሚያገኝ ያረጋግጥልናል።"

ሙስሊሞች በመልካም ጉዳይ እንደሚመካከሩ እንረዳለን። ወንድሙ ችግር እያጋጠመው እንደሆነ የተመለከተ ሰው ያንን ችግር የሚያስወግድበትን ነገር ለርሱ ያቅርብለት።

አዛን እስከሰማ ድረስ ቤት ከመስጂድ መራቁ የጀመዓን ሶላት ለመተው ምክንያት አይሆንም።

التصنيفات

የኢስላም ደረጃና ውበቶቹ