ጀነት ውስጥ ረያን የሚባል በር አለ። የትንሳኤ ቀን ጾመኞች በርሱ በኩል ይገባሉ። በርሱ በኩልም ከነርሱ ውጪ አንድም ሰው አይገባም።

ጀነት ውስጥ ረያን የሚባል በር አለ። የትንሳኤ ቀን ጾመኞች በርሱ በኩል ይገባሉ። በርሱ በኩልም ከነርሱ ውጪ አንድም ሰው አይገባም።

ከሰህል ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: «ጀነት ውስጥ ረያን የሚባል በር አለ። የትንሳኤ ቀን ጾመኞች በርሱ በኩል ይገባሉ። በርሱ በኩልም ከነርሱ ውጪ አንድም ሰው አይገባም። "ጾመኞች የት አሉ?" ይባላል። እነርሱም ይቆማሉ። በርሱ በኩልም ከነርሱ ውጪ አንድም ሰው አይገባም። እነርሱ የገቡ ጊዜ ይዘጋል። በርሱ በኩል ማንም አይገባም።»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከጀነት በሮች መካከል "የረያን በር" ተብሎ የሚጠራ በር እንዳለና የትንሳኤ ቀን በርሱ በኩል ጾመኞች እንደሚገቡበት ተናገሩ። ከነርሱ ውጪም በርሱ በኩል አንድም ሰው እንደማይገባበት፤ "ጾመኞች የት አሉ?" ተብሎም እንደሚለፈፍ፤ ጾመኞችም ተነስተው እንደሚገቡ፤ በርሱ በኩል ከነርሱ ውጪ ማንም እንደማይገባበት፤ የመጨረሻቸው ሰው ከገባ በኃላ እንደሚዘጋና ከዛ በኋላም በርሱ በኩል ማንም እንደማይገባበት ተናገሩ።

فوائد الحديث

ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ የጾምን ደረጃና የጾመኞችን ክብር ያሳየናል።"

አላህ ለጾመኞች ከጀነት ስምንት በሮች መካከል አንድ በር ለብቻቸው አዘጋጅቷል። እነርሱ የገቡ ጊዜም ይዘጋል።

ጀነት በሮች እንዳላት መገለፁን ተረድተናል።

ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "(ጾመኞች የት አሉ?) የሚለው ንግግር ጾም የሚያበዙ የት አሉ? ለማለት ነው። ፍትሃዊ ግፈኛ እንደሚባለው ማለት ነው። ይህ የሚባለውም ልምዱ አድርጎ ለያዘው ሰው ነው እንጂ አንዴ ለፈፀመው ሰው አይደለም።"

(ረያን) ማለት የሚያረካ ማለት ነው። ምክንያቱም ጾመኞች በተለይ በበጋ ቀናት ቀኑ ሀሩራማና ረጅም በሆነበት ጊዜ ሲጾሙ ይጠማሉ። ለነርሱ ብቻ የተለየን ይህ በር "የረያን በር" በሚል በዚህ ስያሜ በመሰየም ይመነዳሉ። ረያን ማለት እጅግ መርካት የጥም ተቃራኒ ማለት ሲሆን በዚህም የተሰየመው ጾመኞች በጥማቸውና በረሃባቸው የሚመነዱበት ስለሆነ ነውም ተብሏል።

التصنيفات

የጾም ትሩፋት