إعدادات العرض
እንዲያ ከሆነ እኔን አታስመስክረኝ! እኔ በበደል ላይ አልመሰክርም።" አሉ።
እንዲያ ከሆነ እኔን አታስመስክረኝ! እኔ በበደል ላይ አልመሰክርም።" አሉ።
ከኑዕማን ቢን በሺር (ረዺየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: «የኑዕማን እናት ቢንት ረዋሓ ለልጇ ኑዕማን ከገንዘቡ የተወሰነ ስጦታ እንዲሰጠው አባቱን ጠየቀችው። አንድ ዓመት ከዘገየ በኋላ ስጦታውን መስጠቱ ላይ ተስማማ። እርሷም "ለልጄ በምትሰጠው ስጦታ የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እስክታስመሰክር ድረስ አልደሰትም።" አለች። እኔም ህፃን ነበርኩኝና አባቴ እጄን ይዞ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ መጣ። እርሱም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የዚህ ልጅ እናቱ ቢንት ረዋሓ ለልጄ በምሰጠው ስጦታ ምስክር እንዳደርጎት ወደደች።" አለ። የአላህም መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "በሺር ሆይ! ከዚህ ልጅ ውጪ ሌላ ልጅ አለህን?" አሉ። እርሱም "አዎን" አለኝ አለ። እርሳቸውም "ለዚህ ልጅ የምትሰጠውን ስጦታ አምሳያ ለሁሉም ሰጥተሃልን?" አሉት። እርሱም "አይ" አለ። እርሳቸውም "እንዲያ ከሆነ እኔን አታስመስክረኝ! እኔ በበደል ላይ አልመሰክርም።" አሉ። በሙስሊም ዘገባ ደሞ "በዚህ ጉዳይ ከኔ ውጪ የሆነን አስመስክር" አሉ።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Hausa Português Kurdî Tiếng Việt অসমীয়া Nederlands Kiswahili සිංහල ไทยالشرح
ኑዕማን ቢን በሺር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እናቱ ዐምረህ ቢንት ረዋሓ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - አባቱ ከገንዘቡ የተወሰነ ስጦታን ለልጇ እንዲሰጥ እንደጠየቀችው ተናገረ። ስለከበደው አንድ አመት ካዘገየ በኃላ ፍላጎቷን በማሟላት ለልጁ ኑዕማን ስጦታ መስጠት ታየው። እርሷም እንዲህ አለች: "ለልጄ በምትሰጠው ስጦታ የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እስክታስመሰክር ድረስ አልወድም።" እኔም በዛን ግዜ ህፃን ነበርኩኝ። አባቴ እጄን ይዞ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ በመምጣት እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ ሆይ! የዚህ ልጅ እናት ቢንት ረዋሓ ለልጇ በምሰጠው ስጦታ እርሶን ማስመስከሬን ወደደች።" እርሳቸውም (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: "በሺር ሆይ! ከዚህ ልጅ ውጪ ሌላ ልጅ አለህን?" እርሱም "አዎን" አለ። እርሳቸውም "ይህን የመሰለ ስጦታ ለሁሉም ልጆችህ ሰጥተሃልን?" አሉት። እርሱም "አይ" አለ። እርሳቸውም "እንዲህ ከሆነ አታስመስክረኝ። እኔ በግፍና በበደል ላይ አልመሰክርም።" አሉ። ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሥ ደግሞ እርሱን በመውቀስ መልኩ "ይልቁን በዚህ በደልህ ከኔ ውጪ ሌላን አስመስክር።" አሉት።فوائد الحديث
በወንድም በሴትም ልጆች መካከል በስጦታ ፍትሃዊ መሆን ግዴታ እንደሆነ እንረዳለን። የግዴታ ወጪ ግን ለሁሉም ልጅ እንደሚያስፈልገው መጠን ነው የሚሰጠው።
አንድ ልጅን ከሌላ ልጅ ማበላለጥ ከግፍና ከበደል የሚመደብ ነው። በዚህ ጉዳይ በመስጠትም ይሁን ሃላፊነት በመውሰድ ላይ ምስክር መሆን አይፈቀድም።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "በልጆች መካከል ስጦታን እኩኩል ማድረግ ተገቢ ነው። ለእያንዳንዱ ሁሉ ለሌላኛው የሰጠውን አምሳያ መስጠት አለበት። አያበላልጥም። በወንድና በሴት መካከልም እኩኩል ማድረግ አለበት። አንዳንድ የመዝሃባችን ዑለሞች: ለወንድ ልጅ ለሴት የሚሰጣትን ሁለት እጅ ይሰጣል። ቢሉም ትክክለኛውና የታወቀው የመዝሃባችን አቋም ግን የዚህ ሐዲሥ ጉልህ መልዕክት እንደሚጠቁመው በሁለቱ መካከል እኩኩል አድርጎ መስጠት ይገባል።"
ከሸሪዓ ተቃራኒ የሚፈፀሙ ህግጋት ውድቅ ይደረጋሉ እንጂ ተፈፃሚ አይደረጉም።
ዳኛና ሙፍቲ ማብራሪያ ለሚፈልግ ጉዳይ ማብራሪያ መጠየቅ አለባቸው። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) "ይህንን ለሁሉም ልጆችህ አድርገሃልን?" ስላሉ ነው።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ወላጅ ለልጁ የሰጠውን ስጦታ ማስመለስ እንደሚፈቀድ ያስረዳናል።"
በወንድማማቾች መካከል ትስስርን የሚፈጥር ማድረግና በመካከላቸው ፀብ የሚፈጥርን ወይም ልጆች ወላጆችን እንዲበድሉ የሚያወርስን መተው መታዘዙን እንረዳለን።
التصنيفات
ለልጆች ቀለብ ማውጣት