አንድ ሰውዬ ዓደን አብየን ላይ ሆኖ እንኳ ሐረም ውስጥ በደል ለመስራት ቢያስብ አላህ አሳማሚ ቅጣትን ያቀምሰዋል።

አንድ ሰውዬ ዓደን አብየን ላይ ሆኖ እንኳ ሐረም ውስጥ በደል ለመስራት ቢያስብ አላህ አሳማሚ ቅጣትን ያቀምሰዋል።

ዐብደላህ ቢን መስዑድ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- ከነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዳስተላለፈው {በእርሱም ውስጥ (ከትክክለኛ መንገድ) በመዘንበል በዳይ ሆኖ (ማንኛውንም ነገር) የሚፈልግ ሰው ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን።} [አልሐጅ: 25] በሚለው የአላህ ንግግር ዙሪያ እንዲህ ብለዋል: "አንድ ሰውዬ ዓደን አብየን ላይ ሆኖ እንኳ ሐረም ውስጥ በደል ለመስራት ቢያስብ አላህ አሳማሚ ቅጣትን ያቀምሰዋል።"

[ሶሒሕ ነው።]

الشرح

ዐብደላህ ቢን መስዑድ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - {በእርሱም ውስጥ (ከትክክለኛ መንገድ) በመዘንበል በዳይ ሆኖ (ማንኛውንም ነገር) የሚፈልግ ሰው ከአሳማሚ ቅጣት እናቀምሰዋለን።} [አልሐጅ: 25] በሚለው የአላህ ቃል ዙሪያ እንዲህ ማለታቸውን ገለፀ: "አንድ ሰው በሐረም መካ ላይ በምላስ ወይም ሆን ብሎ በመግደል አላህ እርም ያደረገው በሚደፈርበት መልኩ መጥፎን ስራ ለመስራት በነፍሱ ቢያስብና ቢቆርጥ ይህን ሊያደርግ የቆረጠው በየመን ከሚገኘው የዓደን ከተማ ሆኖ ቢሆንና ባይሰራው እንኳ በዚህ ምክንያት አላህ በአሳማሚ ቅጣቱ ሊቀጣው የተገባ ይሆናል። ለዚህ ቅጣት ማሰቡ ብቻ በቂ ነው።"

فوائد الحديث

ሐረም ልዩ ስፍራና የላቀ መሆኑን መገለፁ እንረዳለን።

ሰዕዲይ እንዲህ ብለዋል: "በዚህች በተከበረች አንቀፅ ሐረምን ማክበርና እጅግ ማላቅ ግዴታ መሆኑን፤ እንዲሁም ሐረም ውስጥ ሆኖ ወንጀል ማሰብና መስራት መከልከሉን እንረዳለን።"

ዶሐክ እንዲህ ብለዋል: "ሰውዬው ሌላ ምድር ላይ ሆኖ መካ ላይ ወንጀል ለመስራት ቢያስብና ግን ወንጀሉን ባይሰራው እንኳ በርሱ ላይ ወንጀል ይፃፍበታል።"

التصنيفات

የቁርአን አንቀጾች መውረድ ምክንያት