إعدادات العرض
ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም!" "የአላህ መልክተኛ ሆይ ማን ነው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ጎረቤቱ ተንኮሉን ያላመነው ሰው ነው።" አሉ።
ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም!" "የአላህ መልክተኛ ሆይ ማን ነው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ጎረቤቱ ተንኮሉን ያላመነው ሰው ነው።" አሉ።
ከአቡ ሹረይሕ (ረዲየላሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ፦ «"ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም!" "የአላህ መልክተኛ ሆይ ማን ነው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ጎረቤቱ ተንኮሉን ያላመነው ሰው ነው።" አሉ።»
[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪ ዘግበውታል።]
الشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ማሉ። መሃላቸውንም ሶስት ጊዜ አድርገው አፅንዖት ሰጥተው እንዲህ አሉ: "ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም! ወላሂ አላመነም!" አሉ። ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማን ነው ያላመነው?" አሉ። እርሳቸውም "ከክዳቱ፣ ከግፉና ከክፋቱ አንፃር ጎረቤቱ የሚፈራው ነው።" አሉ።فوائد الحديث
ጎረቤቱ ከግፉና ከክፋቱ የማያምኑት ሰው ላይ ኢማን ውድቅ መደረጉ ትልቅ ወንጀል መሆኑንና ኢማኑ የጎደለው መሆኑን ይጠቁማል።
ለጎረቤት መልካምን በመዋል ላይና ጎረቤትን በንግግር ወይም በተግባር ማወክን በመተው ላይ ጠንካራ የሆነ ማነሳሳት መደረጉን እንረዳለን።
التصنيفات
ስምምነትና የጉርብትና ህግጋት