አንዳችሁ ትከሻዎቹ ላይ አንዳችም ነገር የሌለ ሆኖ በአንድ ልብስ ብቻ አይስገድ።

አንዳችሁ ትከሻዎቹ ላይ አንዳችም ነገር የሌለ ሆኖ በአንድ ልብስ ብቻ አይስገድ።

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "አንዳችሁ ትከሻዎቹ ላይ አንዳችም ነገር የሌለ ሆኖ በአንድ ልብስ ብቻ አይስገድ።"»

[ሶሒሕ ነው።] [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በአንድ ልብስ የሰገደ ሰው ሁለት ትከሻዎቹን (ከአንገቱ እስከ ማጅራቱ ያለውን) አንዳች መሸፈኛ በነርሱ ላይ ሳያደርግ ራቁት አድርጎ መስገዱን ከለከሉ። ሁለቱ ትከሻዎች ሀፍረተ ገላ ባይሆኑም እንኳ ሀፍረተ ገላ ሲሸፈኑ አብሮ ለመሸፈን የተመቹ ናቸውና። በሶላት ውስጥ አላህ ፊት ሲቆምም አላህን ለማላቅና ለማክበር የቀረበ ነው።

فوائد الحديث

መሸፈኑ ግዴታ የሆነበትን አካል ከሸፈነ በአንድ ልብስ መስገድ ይፈቀዳል።

በሁለት ልብስ መስገድ እንደሚፈቀድም እንረዳለን። በአንዱ የላይኛውን የሰውነት ክፍሉን ይሸፍናል። በሌላኛው የታችኛውን ሰውነቱ ይሸፍናል።

ሰጋጅ የሆነ ሰው ባማረ ሁኔታ መሆኑ እንደሚወደድ እንረዳለን።

ሶላት ውስጥ ሁለቱን ወይም አንዱን ትከሻ መሸፈን ከቻለ ግዴታ ነው። "ክልከላው ይጠላል ለማለት ነው" ያሉም አሉ።

ከሰሐቦች (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና -አንዳንዶቹ ሁለት ልብስ እንኳን መልበስ በማይችሉበት መልኩ እጅ ያጠራቸው (የገንዘብ እጥረት ያለባቸው) እንደነበሩ እንረዳለን።

ነወዊይ በሐዲሡ ሀሳብ ዙሪያ የሚከተለውን ብለዋል: "የሐዲሡ ጥበብ ትከሻው ላይ ምንም ሳይኖር በአንዱ ልብስ ያሸረጠ ጊዜ ሀፍረተ ገላው አለመገለጡ አያስተማምንም። ይህም የተወሰነውን ልብሱ ትከሻው ላይ ካደረገ ሰው በተቃራኒ ነው። ሽርጥ ብቻ ያደረገ ሰው በእጁ ወይም በሁለት እጆቹ ልብሱን መያዝ ሊጠበቅበት ይችላል። በዚህም ከሶላቱ ተግባር ይልቅ በመያዝ ይጠመዳል፤ ከደረት ስር ቀኝ እጅን ግራ እጅ ላይ ማድረግና እጆችን ከፍ ማድረግ ሱና በሆነባቸው ቦታዎች ላይ ከፍ የማድረጉ ሱናና ሌሎችም ሱናዎች ያመልጠዋል። እንዲሁም የሰውነትን የላይኛውን ክፍልና የውበት ቦታን ከመሸፈን መተውም ስላካተተ ነው። አላህ እንዲህ ብሎ ሳለ: {(ሀፍረተ ገላችሁን የሚሸፍኑትን) ጌጦቻችሁን በመስገጃው ሁሉ ዘንድ ያዙ!} [አልአዕራፍ: 31]"

التصنيفات

የሶላት መስፈርቶች