إعدادات العرض
ሰዎች በመስጂድ ጉዳይ ሳይፎካከሩ ሰዓቲቱ አትቆምም።
ሰዎች በመስጂድ ጉዳይ ሳይፎካከሩ ሰዓቲቱ አትቆምም።
ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል: "ሰዎች በመስጂድ ጉዳይ ሳይፎካከሩ ሰዓቲቱ አትቆምም።"
[ሶሒሕ ነው።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Hausa Kurdî Русский Tiếng Việt Magyar ქართული සිංහල Kiswahili Română অসমীয়া ไทย Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ከትንሳኤ ቀን መቅረብና የዱንያ መጠናቀቅ ምልክቶች መካከል አንዱ ሰዎች መስጂዶችን በማስዋብ መፎካከራቸው ነው። ወይም አላህን ከማውሳት ውጪ ለሌላ አላማ ባልተገነቡ መስጂዶች ውስጥም በዱንያቸው መፎካከራቸው ነው።فوائد الحديث
በመስጂዶች መፎካከር ክልክል መሆኑን እንረዳለን። ለአላህ ተብሎም ስላልተሰራ ተቀባይነት የሌለው ስራ ነው።
በቀለም፣ በቅርፃ ቅርፅና በጽሑፎች መስጂዶችን ማስጌጥ መከልከሉን እንረዳለን። ይህም ሰጋጆችን ሲመለከቱት ስለሚያዘናጋቸው ነው።
ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: "የዚህን ሐዲሥ እውነተኝነት ዛሬ ላይ መታየቱ ምስክር ይሆንልናል። እርሱም ከነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - አስደናቂ ተአምራቶች መካከል አንዱ ነው።"
التصنيفات
የመስጊዶች ህግጋት