إعدادات العرض
አንዳችሁ ለብቻው የሚሰግደውን ሶላት የህብረት ሶላት በሃያ አምስት ክፍል (እጥፍ) ይበልጠዋል። የምሽት መልአክቶችና የቀን መልአክቶች በፈጅር ሶላት ወቅት ይገናኛሉ።
አንዳችሁ ለብቻው የሚሰግደውን ሶላት የህብረት ሶላት በሃያ አምስት ክፍል (እጥፍ) ይበልጠዋል። የምሽት መልአክቶችና የቀን መልአክቶች በፈጅር ሶላት ወቅት ይገናኛሉ።
ከአቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም - የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦ "አንዳችሁ ለብቻው የሚሰግደውን ሶላት የህብረት ሶላት በሃያ አምስት ክፍል (እጥፍ) ይበልጠዋል። የምሽት መልአክቶችና የቀን መልአክቶች በፈጅር ሶላት ወቅት ይገናኛሉ።" ቀጥሎም አቡ ሁረይራ እንዲህ አለ: ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ {የጎህ ሶላት ( መላእክት) የሚጣዱት ነውና።} [አልኢስራእ:78]»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Türkçe اردو हिन्दी Tagalog 中文 Kurdî Português Tiếng Việt Kiswahili Nederlands অসমীয়া ગુજરાતી සිංහල Magyar ქართული Hausa Română ไทย తెలుగు मराठी ភាសាខ្មែរ دریالشرح
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሰውዬው ከኢማም ጋር በህብረት የሚሰግደው ሶላት ምንዳና አጅሩ ቤቱ ወይም ሱቁ ውስጥ ብቻውን ከሚሰግደው ሃያ አምስት ሶላት እንደሚበልጥ ገለፁ። ቀጥለው ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የምሽትና የቀን መልዐክቶች በፈጅር ሶላት ወቅት እንደሚሰባሰቡ አወሱ። ቀጥሎም አቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዐንሁ ይህንን ለማመሳከር እንዲህ አለ: ከፈለጋችሁ ይህንን አንብቡ: {የጎህ ሶላት (መላእክት) የሚጣዱት ነውና።} [አልኢስራእ:78] ማለትም: የፈጅር ሶላት የምሽት መልአክቶችና የቀን መልአክቶች የሚገኙበት ነው ማለት ነው።فوائد الحديث
ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ኢብኑ ደቂቅ አልዒድ እንዳሉት በህብረትም ይሁን በተናጠል ቤት ውስጥም ይሁን ሱቅ ውስጥ ከሚሰገድ ሶላት በመስጂድ ውስጥ የሚሰገድ የህብረት ሶላት ምንዳ ይበልጣል።"
ይህ ሐዲሥ የፈጅር ሶላት መልዐክቶች የሚሰባሰቡባት በመሆን ብቸኛ መሆኗን በመግለፁ የፈጅር ሶላትን ደረጃ ያስረዳናል።
ኢብኑ ባዝ እንዲህ ብለዋል: "አንድ አማኝ ይህን ትልቅ መልካም ነገር ለማግኘት ቤቱ ከመስጂድ ቢርቅ እንኳ ሶላትን በህብረት መስገድን በመጠባበቅ ላይ መጣር ይገባዋል።"
ነወዊይ የህብረት ሶላት ለብቻ ከሚሰገድ ሶላት በሀያ አምስት ደረጃ ይበልጣል የሚሉ ዘገባዎችን በሀያ ሰባት ደረጃ ይበልጣል ከሚሉ ዘገባዎች ጋር ሲያስማሙ እንዲህ አሉ: "በሁለቱ ዘገባዎች መካከል የምናስታርቀው በሶስት መልኩ ነው። የመጀመሪያው: በሁለቱ ዘገባዎች መካከል ምንም መጋጨት የለም። ትንሹ መጠቀሱ ብዙውን ውድቅ አያደርግምና። የኡሱል ምሁራን ዘንድ ከቁጥር የምንወስደው ግንዛቤ መሰረት አይሆንም የሚል መርህ አላቸውና። ሁለተኛው: መጀመሪያ የተናገሩት ትንሹን ነበር። ከዚያም አላህ ተጨማሪ ደረጃውን አሳወቃቸውና ተናገሩት በሚል ልናስታርቃቸው እንችላለን። ሶስተኛው: ሶላቱና ሰጋጆቹ እንደመለያየታቸው ምንዳውም ይለያያል። ሶላቱን እንደማሟላታቸው፤ አፈፃፀሙንና ተመስጦውን እንደመጠበቃቸው፤ የጀመዓው ቁጥር እንደመብዛቱና ደረጃቸው የላቁ ሰዎች እንደመኖራቸው፤ እንደቦታው ልቅናና የመሳሰሉት መለያዎች አንዳንዱ ሀያ አምስት ይኖረዋል አንዳንዱ ደግሞ ሀያ ሰባት ይኖረዋል በሚል እናስታርቃለን። አላህ ይበልጡን ያውቃል።"
التصنيفات
የጀማዓህ ሶላት ትሩፋትና ህግጋት