إعدادات العرض
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስሩ ቀናት የገቡ ጊዜ ሌሊቱን ህያው ሆነው ያሳልፋሉ፤ ቤተሰባቸውንም ያነቃሉ፤ ይበረቱና…
የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስሩ ቀናት የገቡ ጊዜ ሌሊቱን ህያው ሆነው ያሳልፋሉ፤ ቤተሰባቸውንም ያነቃሉ፤ ይበረቱና ሽርጣቸውንም ያጠብቁ ነበር።
ከአማኞች እናት ከዓኢሻ - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስሩ ቀናት የገቡ ጊዜ ሌሊቱን ህያው ሆነው ያሳልፋሉ፤ ቤተሰባቸውንም ያነቃሉ፤ ይበረቱና ሽርጣቸውንም ያጠብቁ ነበር።"
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी ئۇيغۇرچە Kurdî Português සිංහල Kiswahili অসমীয়া Tiếng Việt ગુજરાતી Hausa Nederlands മലയാളം ไทย Românăالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስሩ ቀናት የገቡ ጊዜ ምሽቱን ሁሉ በተለያዩ አምልኮዎች ህያው ሆነው ያሳልፉ ነበር። ቤተሰባቸውንም ለሶላት ይቀሰቅሱ ነበር። ከልማዳቸው ተጨማሪ በሆነ መልኩ በአምልኮ ይታገሉ ነበር። ከሚስቶቻቸው ጋር መተኛትንም ትተው በአምልኮ ብቻም ያሳልፉ ነበር።فوائد الحديث
በላጭ የሆኑ ወቅቶችን በመልካም ስራ ላይ ሆነን እንድናሳልፍ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ በረመዷን የመጨረሻ አስሩ ቀናቶች አምልኮ መጨመርና ሌሊቱንም በአምልኮ ህያው ሆኖ ማሳለፍ እንደሚወደድ ያስረዳናል።"
አንድ ባሪያ ቤተሰቦቹን ወደ አምልኮ በማዘዝ ላይ ጥረት ሊያደርግና በዛም ላይ ሊታገስ ይገባዋል።
መልካም ተግባራትን መስራት ቆራጥነትን፣ ትግስትንና መበረታታትን ይፈልጋል።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ዑለማዎች (ሽርጣቸውን ያጠብቁ ነበር) በሚለው ትርጉም ዙሪያ የተለያየ ሃሳብ አላቸው። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከሌላው ጊዜ በተለየ ልምዳቸው ጨምረው በማምለክ መታገላቸውን ለመግለፅ ነው፤ ያሉም አሉ። ትርጉሙ ለአምልኮ መታጠቃቸው ነው። "ለዚህ ጉዳይ ሽርጤን አጠበቅኩኝ።" ሲባል ለርሱ ታጠቅኩኝ ተዘጋጀሁ ማለት ነው፤ ያሉም አሉ። በአምልኮ ለመጠመድ ሴቶችን መራቃቸውን ለመግለፅ የተጠቀሙት ቃል ነውም ተብሏል።
التصنيفات
የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት