إعدادات العرض
ሶስት ጁመዓዎችን በመሳነፍ የተወ ሰው አላህ ልቡ ላይ ያሽግበታል።
ሶስት ጁመዓዎችን በመሳነፍ የተወ ሰው አላህ ልቡ ላይ ያሽግበታል።
ከአቢ ጀዕድ አድዶምሪይ ረዺየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - (ከነቢዩ ሶሓቦች መካከልም አንዱ ነበር) እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "ሶስት ጁመዓዎችን በመሳነፍ የተወ ሰው አላህ ልቡ ላይ ያሽግበታል።"
[ሶሒሕ ነው።]
الترجمة
العربية Tiếng Việt Bahasa Indonesia Nederlands Kiswahili অসমীয়া English ગુજરાતી සිංහල Magyar ქართული Hausa Română ไทย Português मराठी ភាសាខ្មែរ دری বাংলা Kurdîالشرح
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- የጁሙዓን ሶላት ከመተው አስጠነቀቁ። ሶስት ጊዜ የጁመዓን ሶላቶች ያለምንም በቂ ምክንያት በመሳነፍና በመዘናጋት የተወ ሰው አላህ መልካም ነገር ወደርሱ እንዳይደርስ በመከልከል ቀልቡን ያሽገዋልም ከመልካም ነገር ይጋርደዋልም።فوائد الحديث
ኢብኑል ሙንዚር የጁሙዓ ሶላት የነፍስ ወከፍ ግዴታ በመሆኑ ላይ የዑለሞች ስምምነት እንዳለ አውስተዋል።
የጁመዓን ሶላት በስንፍና በተወ ሰው ላይ አላህ ልቡን እንደሚያሽግ ዛቻ መምጣቱን እንረዳለን።
ጁሙዓን በቂ ምክንያት ኖሮት የተወ ሰው ይህ ዛቻ ውስጥ አይካተትም።
ሸውካኒይ እንዲህ ብለዋል: "(ሶስት ጁሙዓዎች) ማለታቸው ጁሙዓዎቹ ተከታትለውም ሆነ ተበታትነው በጥቅሉ ከተተዉ በየዓመቱ አንድ አንድ ጁመዓ ቢተው እንኳ ከሶስተኛዋ በኋላ አላህ ቀልቡን ያሽጋል ማለት ሊሆንም ይችላል። የሒዲሡ ግልፅ መልዕክትም ይኸው ነው። ሶስት ተከታታይ ጁሙዓዎች ማለት ተፈልጎበት ሊሆንም ይችላል።"
التصنيفات
Virtue of Friday