إعدادات العرض
እነሆ የሚዋሹና ግፈኛ የሆኑ መሪዎች ይመጣሉ። ውሸታቸውን አምኖ የተቀበለና በበደላቸው ላይ ያገዛቸው እርሱም ከኔ አይደለም። እኔም ከርሱ አይደለሁም።
እነሆ የሚዋሹና ግፈኛ የሆኑ መሪዎች ይመጣሉ። ውሸታቸውን አምኖ የተቀበለና በበደላቸው ላይ ያገዛቸው እርሱም ከኔ አይደለም። እኔም ከርሱ አይደለሁም።
ከሑዘይፋህ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል: "እነሆ የሚዋሹና ግፈኛ የሆኑ መሪዎች ይመጣሉ። ውሸታቸውን አምኖ የተቀበለና በበደላቸው ላይ ያገዛቸው እርሱም ከኔ አይደለም። እኔም ከርሱ አይደለሁም። ወደኔ ምንጭም (ወደ ሐውድ) አይመጣም። የነርሱን ውሸት አምኖ ያልተቀበለና በበደላቸውም ላይ ያላገዛቸው ሰው ደሞ እርሱ ከኔ ነው። እኔም ከርሱ ነኝ። ወደኔ ምንጭ (ሐውድም) ይመጣል።"
الترجمة
العربية Tiếng Việt Bahasa Indonesia Nederlands Kiswahili English অসমীয়া ગુજરાતી සිංහල Magyar ქართული Hausa Română ไทย Português मराठी ភាសាខ្មែរ دری বাংলা Kurdîالشرح
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እርሳቸው ከሞቱ በኋላ ሲናገሩ የሚዋሹ፣ የማይሰሩትን የሚናገሩና በፍርዳቸው የሚበድሉ መሪዎች በሰዎች ላይ እንደሚሾሙ፤ ወደነርሱ ስራ ገብቶ ውሸታቸውን አምኖ የተቀበለ ወይም ወደነርሱ ለመቃረብ በሚልና እነርሱ ዘንድ ያለውን በመከጀል ለነርሱ የሚመቻቸውን ፈትዋ እንደመስጠት የመሰለ በሚሰሩት ወይም በሚናገሩት በደል ላይ ያገዛቸው እኔ ከርሱ የጠራሁ ነኝ። እርሱም ከኔ አይደለም። እኔም ከርሱ አይደለሁም። የትንሳኤ ቀንም የከውሠርን ምንጭ ሳጠጣ ወደኔ አይመጣም። ወደነርሱ ተግባር ያልገባ፤ ውሸታቸውን ያልተቀበለና በበደላቸው ላይም ያላገዛቸው እርሱ ከኔ ነው። እኔም ከርሱ ነኝ። የትንሳኤ ቀንም ወደ (ሐውድ) ምንጬ ይመጣል ብለው ተናገሩ።فوائد الحديث
ምክር ለመስጠት፣ ለማስተካከልና ክፋታቸውን ለመቀነስ ወደ ባለስልጣኖች መግባት የሚፈለግ ጉዳይ ነው። ነገር ግን በግፍ ላይ ሊያግዛቸውና ውሸታቸውን ሊያምንላቸው ወደነርሱ ከገባ ይህ የተወገዘ ተግባር ነው።
መሪን በበደሉ ላይ የተባበረ ሰው የሚደርስበት ቅጣት መገለፁ፤
ይህ ሐዲሡ ውስጥ የመጣው ዛቻ ይህ ድርጊት ክልክል መሆኑንና ከትላልቅ ወንጀሎች መሆኑን ይጠቁማል።
በበጎና አላህን በመፍራት ላይ መተባበር ላይ መነሳሳቱን፤ በወንጀልና ወሰን በማለፍ ላይ ከመተባበርም መቆጠብ እንደሚገባ እንረዳለን።
ለነቢያችን ሙሐመድ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ሐውድ (ምንጭ) እንደሚሰጣቸውና ኡመታቸውም ከምንጯ ለመጠጣት እንደሚወርዱ መረጋገጡን እንረዳለን።