ከናንተ መካከል እውነታን ተመልክቶ ወይም አውቆ ከመናገር ማናችሁንም ቢሆን ለሰዎች ያለው ፍራቻ እንዳይከለክለው።

ከናንተ መካከል እውነታን ተመልክቶ ወይም አውቆ ከመናገር ማናችሁንም ቢሆን ለሰዎች ያለው ፍራቻ እንዳይከለክለው።

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ ብለዋል፦ "ከናንተ መካከል እውነታን ተመልክቶ ወይም አውቆ ከመናገር ማናችሁንም ቢሆን ለሰዎች ያለው ፍራቻ እንዳይከለክለው።"

[ሶሒሕ ነው።] [ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በባልደረቦቻቸው መካከል ኹጥባ አደረጉ። ከመከሯቸው ጉዳዮችም አንዱ የትኛውም ሙስሊም እውነትን ተመልክቶ ወይም አውቆ ከመናገርና በርሱ ከማዘዝ ሰዎችንና ሀይላቸውን መፍራትና መስጋት እንዳይከለክለው ነው።

فوائد الحديث

እውነትን ግልፅ በማድረግና ሰዎችን ፍራቻ እውነትን ባለመሸሸግ ዙሪያ መነሳሳቱን እንረዳለን።

እውነትን መናገር ማለት በአነጋገር መንገዱ ስርአትን፣ ጥበብንና በመልካም መልኩ መገሰፅን አይተግብር ማለትን አያሲዝም።

መጥፎን ማውገዝና ከአላህ ሐቅ ጋር ከሚጋጭ የሰዎች ጥቅም የአላህን ሐቅ ማስቀደም ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።

التصنيفات

በመልካም የማዘዝና ከመጥፎ የመከልከል ፍርድ