إعدادات العرض
ሰዎች በመክሰሳቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም (ለመውሰድ) ይከሱ ነበር። ነገር ግን ማስረጃ በከሳሽ ላይ፣ መሀላ ደግሞ ክሱን ባወገዘ ሰው ላይ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው…
ሰዎች በመክሰሳቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም (ለመውሰድ) ይከሱ ነበር። ነገር ግን ማስረጃ በከሳሽ ላይ፣ መሀላ ደግሞ ክሱን ባወገዘ ሰው ላይ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ተደረገ።
ከኢብኑ ዐባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል: "ሰዎች በሙግታቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም (ለመውሰድ) ይሞግቱ ነበር። ነገር ግን ማስረጃ በከሳሽ ላይ፣ መሀላ ደግሞ ክሱን ባወገዘ ሰው ላይ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ተደረገ።"
[ሐሰን ነው።] [رواه البيهقي وغيره هكذا وبعضه في الصحيحين]
الترجمة
العربية Español English اردو Indonesia বাংলা Français Türkçe Русский Bosanski සිංහල हिन्दी 中文 فارسی Tiếng Việt Tagalog Kurdî Hausa Português മലയാളം తెలుగు Kiswahili தமிழ் မြန်မာ ไทย Deutsch پښتو অসমীয়া Shqip Nederlands ગુજરાતી Кыргызча नेपाली Lietuvių دری Српски тоҷикӣ Kinyarwanda Magyar Čeština Moore Malagasy Oromoo ಕನ್ನಡ Wolof Azərbaycan O‘zbek Українська ქართული Македонски ភាសាខ្មែរ ਪੰਜਾਬੀ मराठी Kirundi Kurmancî Bahasa Melayuالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሰዎች ያለማስረጃና ያለ ጠቋሚ ማስረጃ በመክሰሳቸው ብቻ ቢሰጣቸው ኖሮ ሰዎች የሌሎችን ገንዘብና ደም ለመውሰድ ይከሱ እንደነበር፤ ነገር ግን ከሳሽ ለፈለገው ጉዳይ ማስረጃ የማስቀደም ግዴታ እንዳለበት ማስረጃ ከሌለው ደግሞ ክሱ ወደ ተከሳሽ ይቀርብና ክሱን ካወገዘው በመማል ራሱን ከጥፋተኝነት እንደሚያነፃ ገለፁ።فوائد الحديث
ኢብኑ ደቂቅ አልዒዲ እንዲህ ብለዋል: «ይህ ሐዲሥ ከህግጋቶች መሰረት መካከል አንዱ መሰረትና በንትርክና መካሰስ ወቅት የምንጠቀመው ትልቅ ምንጭ (መመለሻ) ነው።»
ሸሪዓ የሰዎችን ገንዘብና ደም ከመጫወቻነት ለመጠበቅ የመጣ እንደሆነ እንረዳለን።
ዳኛ በእውቀቱ አይፈርድም። ይልቁንም ፍርድ የሚመለሰው ወደ ማስረጃ ነው።
ማንኛውንም ሙግት የሞገተና ሙግቱ ከማስረጃ የፀዳ ከሆነ ተመላሽ ነው። ይህም በመብቶችም፣ በግብይይትም ይሁን በኢማንና እውቀት ዙሪያም የሚሰራ መርህ ነው።
التصنيفات
ሙግትና ማስረጃ