إعدادات العرض
እነሆ የእሳት ጌታ ካልሆነ በቀር ማንም በእሳት መቅጣት አይገባውም።" አሉ።
እነሆ የእሳት ጌታ ካልሆነ በቀር ማንም በእሳት መቅጣት አይገባውም።" አሉ።
ከኢብኑ መስዑድ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፡- «ጉዞ ላይ ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ነበርን። እርሳቸው ለመፀዳዳት ሄዱ። እኛም ትንሽዬን ወፍ ከነሁለት ጫጩቶቿ ተመለከትንና ጫጩቶቿን ወሰድን። ወፏም ክንፏን እያራገበች በራ መጣች። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - እንዲህ አሉ: "ይህቺን ወፍ ልጆቿን ወስዶ ያስደነገጣት ማነው? ልጆቿን መልሱላት።" ጉንዳኖች ወረውት በእሳት ያቃጠልነውን ስፍራም ተመልክተው እንዲህ አሉ: "ይህንንስ ያቃጠለው ማነው?" እኛም "እኛ ነን።" አልን። እርሳቸውም: " እነሆ የእሳት ጌታ ካልሆነ በቀር ማንም በእሳት መቅጣት አይገባውም።" አሉ።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල Hausa Kurdî Magyar ქართული Kiswahili Română অসমীয়া ไทย Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
ዐብደላህ ቢን መስዑድ - አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንዳወሱት ጉዞ ላይ ከነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ሳሉ ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለመፀዳዳት ሄዱ። ሶሓቦችም ትንሽዬ ወፍ ከነሁለት ጫጩቶቿ አገኙና ጫጩቶቹን ይዘው ሄዱ። ወፏም ጫጩቶቿን በማጣት ድንጋጤ ክንፏን እያራገበችና ዘርግታ እየበረረች መጣች። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - መጡና እንዲህ አሉ: ማነው ልጆቿን በመውሰድ ያሳዘናትና ያስፈራራት? ቀጥሎ እንዲመለሱላት አዘዙ። ቀጥለው በእሳት የተቃጠለ ጉንዳኖች የወረሩት ስፍራ ተመለከቱ። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "ማነው ይህንን ያቃጠለው?" አሉ። አንዳንድ ሶሓቦችም "እኛ ነን።" አሉ። እርሳቸውም "እሳትን ከፈጠረው ከአላህ በቀር አንድም ሰው በህይወት ያለን በእሳት ሊቀጣ አይፈቀድለትም።" አሉ።فوائد الحديث
ለመፀዳዳት ደበቅ ማለት የተደነገገ ተግባር እንደሆነ እንረዳለን።
እንስሳዎችን ልጆቻቸውን በመንጠቅ ከመቅጣት መከልከሉን እንረዳለን።
ጉንዳንና ነፍሳትን በእሳት ከማቃጠል መከልከሉን እንረዳለን።
ለእንስሳዎች በማዘንና በመራራት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። በዚህም እስልምና ቀዳሚ መሆኑን እንረዳለን።
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለእንስሳዎች የነበራቸው እዝነት መገለፁ፤
በእሳት መቅጣት አላህ ብቻ የተነጠለበት ጉዳይ እንደሆነም እንረዳለን።