إعدادات العرض
እነዚህ መስጂዶች ለዚህ ሽንትና ቆሻሻ አይበጁም። እነዚህ የሚበጁት አላህን ለማውሳት፣ ለሶላትና ቁርአንን ለመቅራት ነው።
እነዚህ መስጂዶች ለዚህ ሽንትና ቆሻሻ አይበጁም። እነዚህ የሚበጁት አላህን ለማውሳት፣ ለሶላትና ቁርአንን ለመቅራት ነው።
ከአነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «እኛ ከአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጋር ተቀምጠን ሳለ ድንገት አንድ የገጠር ሰው መጣና መስጂድ ውስጥ መሽናት ጀመረ። የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ባልደረቦችም "አተ! አተ!" አሉት። የአላህ መልክተኛም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "አታቋርጡት ተዉት!" አሉ። ሸንቶ እስኪያጠናቅቅም ተዉት። ቀጥሎ የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጠሩትና እንዲህ አሉት: "እነዚህ መስጂዶች ለዚህ ሽንትና ቆሻሻ አይበጁም። እነዚህ የሚበጁት አላህን ለማውሳት፣ ለሶላትና ቁርአንን ለመቅራት ነው።" አሉት። ወይም የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ይህን የመሰለ ንግግር ተናገሩት። አንድን ሰው ውሃ የሞላ ባልዲ ይዞ እንዲመጣ አዘዙና እላዩ ላይ ደፉበት።»
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Bahasa Indonesia Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Français Hausa Kurdî Русский Tiếng Việt Magyar ქართული සිංහල Kiswahili Română অসমীয়া ไทย Português मराठी دری ភាសាខ្មែរالشرح
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - መስጂዳቸው ውስጥ ከባልደረቦቻቸው ጋር ነበሩ። አንድ ባላገር ከገጠር መጣና የመስጂዱ ጎን ዘንድ ተቀምጦ መሽናት ጀመረ። ሶሓቦችም "አተ አቁም! ተው!" በማለት አስጠነቀቁት። ነቢዩም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - "ተዉት! ሽንቱን አታቋርጡት።" አሉ። እስኪያጠናቅቅም ድረስ ተዉት። ከዚያም ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጠርተው እንዲህ አሉት: መስጂዶች ለሽንትና ለቆሻሻ አይነቶች አይበጁም። መስጂድ የሚበጀው አላህን ለማውሳት፣ ለሶላት፣ ቁርአንን ለመቅራትና ለመሳሰሉት ነው። ቀጥለው ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - አንድን ሶሓባ በውሃ የተሞላ ባልዲ ይዞ እንዲመጣ አዘዙና በቀላሉ ሽንቱ ላይ ደፉበት።فوائد الحديث
መስጂዶችን ማላቅና ለመስጂድ የማይመጥኑ ከሆኑ ነገሮች መጠበቅ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ከዚህ ሐዲሥ መስጂዶችን መጠበቅ፣ ከቆሻሻና አክታ ማፅዳት፣ ከጭቅጭቅ፣ ድምፅን ከፍ ከማድረግ፣ ከመሸጥ፣ ከመግዛት፣ ሌሎችንም ውሎች ከመዋዋልና ተመሳሳይ የሆኑ ነገሮችን ከመፈፀም መራቅ እንደሚገባ እንረዳለን።"
ለአላዋቂ ማዘንና ስህተቱ በንቀትና በትዕቢት የመጣ ካልሆነ በቀር የፈፀመውን ሳያጥላሉና ሳያውኩ ማስተማር እንደሚገባ እንረዳለን።
ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - አዛኝ አስተማሪ፣ ሩሕሩሕ አደብ የሚያሲዙ፣ ቻይ ሆነው የሚያንፁ ነበሩ።
የአላህን ቤቶች በሶላት፣ ቁርአንን በመቅራትና አላህን በማውሳት ማሳመር ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
التصنيفات
የመስጊዶች ህግጋት