إعدادات العرض
ለርሱ (ለኡዱሒያ) የሚታረድ እርድ ያለው ሰው የዙልሒጃ ጨረቃ የወጣች ጊዜ ኡዱሒያውን እስኪያርድ ድረስ ከፀጉሩም ይሁን ከጥፍሩ አንዳችም እንዳይቆርጥ።
ለርሱ (ለኡዱሒያ) የሚታረድ እርድ ያለው ሰው የዙልሒጃ ጨረቃ የወጣች ጊዜ ኡዱሒያውን እስኪያርድ ድረስ ከፀጉሩም ይሁን ከጥፍሩ አንዳችም እንዳይቆርጥ።
የነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሚስትና የአማኞች እናት ከሆነችው ከኡሙ ሰለማ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው እንዲህ አለች: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ አሉ: "ለርሱ (ለኡዱሒያ) የሚታረድ እርድ ያለው ሰው የዙልሒጃ ጨረቃ የወጣች ጊዜ ኡዱሒያውን እስኪያርድ ድረስ ከፀጉሩም ይሁን ከጥፍሩ አንዳችም እንዳይቆርጥ።"
[ሶሒሕ ነው።] [ሙስሊም ዘግበውታል።]
الترجمة
العربية বাংলা Bosanski English Español فارسی Français Bahasa Indonesia Русский Tagalog Türkçe اردو 中文 हिन्दी Tiếng Việt සිංහල Kurdî Português Kiswahili অসমীয়া ગુજરાતી Nederlands Hausa മലയാളം Românăالشرح
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ኡዱሒያን ማረድ የፈለገ ሰው የዙልሒጃ ጨረቃ ግልፅ የሆነ ጊዜ ኡዱሒያውን እስኪያርድ ድረስ ከጭንቅላቱ ወይም ከብብቱ ወይም ከቀድሞ ቀመሱ ወይም ከሌላ አካሉ ላይ ያለን ፀጉርና የእጁን ወይም የእግሩን ጥፍርም እንዳይቆረጥ አዘዙ።فوائد الحديث
አስሩ የዙልሒጃ ቀናት ከገቡ በኋላ ኡዱሒያን ማረድ የነየተ (ያሰበ) ሰው ከነየተበት ጊዜ አንስቶ ኡዱሒያውን እስኪያርድ ድረስ የተጠቀሱትን ነገሮች ከመፈፀም መቆጠብ ይጀምራል።
በመጀመሪያው የማረጃ ቀን ካላረደ በፈለገው የአያመ ተሽሪቅ (ከበዐሉ ቀጥለው ያሉ ሦስት ቀናት ዙልሒጃ 12፣ 12 እና 13) ቀን እስኪያርድ ድረስ እነዚህን አካላቶች ከመቁረጥ እንደተቆጠበ ይቆያል።
التصنيفات
ኡዹሒያ (የዒደል አዽሓ እርድ)