ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በፋንዲያ ወይም በአጥንት ኢስቲንጃእ (ከተፀዳዱ በኋላ ከማዳረቅ) ከለከሉ።

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በፋንዲያ ወይም በአጥንት ኢስቲንጃእ (ከተፀዳዱ በኋላ ከማዳረቅ) ከለከሉ።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - በፋንዲያ ወይም በአጥንት ኢስቲንጃእ (ከተፀዳዱ በኋላ ከማዳረቅ) ከለከሉ። "ሁለቱም አያፀዱም።" ብለዋል።»

[ሶሒሕ ነው።] [ዳረቁጥኒይ ዘግበውታል።]

الشرح

ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና - ከሸና ወይም ሰገራውን ከተጠቀመ በኋላ በእንስሶች አጥንት ወይም በፍጋቸውና በፋንዲያቸው ከማደራረቅ ከለከሉ። እንዲህም አሉ: እርሷ ነጃሳን አታስወግድምም አታፀዳምም።

فوائد الحديث

አንዳንድ የመፀዳዳትና የኢስቲንጃእ ስነስርዓት መገለፁ።

በፋንዲያ (ፍግ) ኢስቲጅማር ማድረግ መከልከሉን እንረዳለን። ይህም ወይ ነጃሳ ስለሆነ ነው ወይም የጂን እንስሶች ቀለብ ስለሆነ ነው።

በአጥንት ኢስቲጅማር ማድረግ መከልከሉን እንረዳለን። ይህም ወይ ነጂስ ነው። ወይም ለጂኖች ምግብ ስለሆነ ነው።

التصنيفات

የመፀዳጃ ቤት ስነ-ስርዓት